ሲዳማ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ሲዳማ ቡና 0-1 ቅዱስ ጊዮርጊስ
36′ ሳላዲን ሰኢድ

ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

89′ ሲዳማ ቡናዎች የአቻነት ግብ ለማግኘት ጫና ፈጥረው እየተጫወቱ ነው፡፡

85′ ናትናኤል ዘለቀ በግምት ከ40 ሜትር የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጣበት፡፡

83′ አዳነ ግርማ ወጥቶ ምንያህል ተሾመ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
74′ አለማየሁ ሙለታ ወጥቶ አስተ፡ቻለው ታመነ ገብቷል፡፡

69′ ተስፋዬ አለባቸው ግልፅ የግብ ማስቆጠር አጋጣሚ አግኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና
68′
አንዱአለም ንጉሴ ወጥቶ በረከት አዲሱ ገብቷል፡፡

50′ ሲዳማ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት እያደረጉ ነው ጊዮርጊስ በአንፃሩ ጊዮርጊሶች ጨዋታውን ለማረጋጋት እየጣሩ ነው፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

– – – –
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነት ተጠናቋል፡፡

45′ የመጀመርያው 45 መደበኛ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

ቢጫ ካርድ
41′
ሳላዲን ፊሽካ ከተነፋ በኀላ ኳስ በመምታቱ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተሰጥቶታል፡፡

ጎልልልል – ቅዱስ ጊዮርጊስ
36′ ሳላዲን ሰኢድ ሁለት ተጫዋቾችን በማለፍ መሬት ለመሬት መትቶ ጊዮርጊስን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

30′ በጥሩ ቅብብል ወደ ጊዮርጊስ የግብ ክልል በመድረስ ወሰኑ ማዜ የሞከረው ኳስ የግቡን ቋሚ ታኮ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና
19′
ለአለም ብርሃኑ (ጉዳት) ወጥቶ ፍቅሩ ወዴሳ ገብቷል፡፡

16′ ለአለም ብርሃኑ ከ16.50 ክልል ውጪ ሳላዲን ላይ በሰራው ፋውል የቅጣት ምት ተሰጥቷል፡፡ ለአለም እጁ ላይ ጉዳት ያጋጠመው ይመስላል፡፡

14′ ፍፁም ተፈሪ ከርቀት ሞክሮ ኦዶንካራ ይዞበታል፡፡

ቢጫ ካርድ
8′
ምንተስኖት አዳነ የመጀመርያውን የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

6′ አዲስ ግደይ ከርቀት የመታውን ኳስ ኦዶንካራ ይዞበታል፡፡

5′ ጨዋታው በመሃል ሜዳ ኳስ በማንሸራሸር እና የተጋጣሚን አጨዋወት በማጥናት ላይ የተመሰረተ ሆኗል፡፡

ተጀመረ!!!
ጨዋታው በ1 ደቂቃ የህሊና ፀሎት እና ብሄራዊ መዝሙር ተጀምሯል፡፡

ሁለቱም ቡድኖች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡

የሲዳማ ቡና አሰላለፍ

ለአለም ብርሃኑ
ዘነበ ከበደ – አንተነህ ተስፋዬ – አወል አብደላ – ሳውሬል ኦልሪሽ
ወሰኑ ማዜ – ፍፁም ተፈሪ – አሳምነው ዘንጀሎ – ተመስገን ካስትሮ – አዲስ ግደይ
አንዱአለም ንጉሴ

የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ

ሮበርት ኦዶካራ
አለማየሁ ሙለታ – ደጉ ደበበ – አይዛክ ኢዜንዴ አበባው ቡታቆ
ተስፈዬ አለባቸው – ምንተስኖት አዳነ
በሀይሉ አሰፋ – አዳነ ግርማ – ራምኬል ሎክ
ሳላዲን ሰኢድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *