ኢትዮጵያ ቡና 1-0 መከላከያ
52′ ያቡን ዊልያም (ፍቅም)
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 5 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
የተጫዋች ለውጥ ኢትዮጵያ ቡና
82′ አማኑኤል ዮሃንስ ወጥቶ ኢኮ ፌቨ ገብቷል፡፡
74′ ሳዲቅ ሴቾ ከተከላካዮች አምልጦ ጥሩ የግብ እድል ቢያገኝም ተከላካዮች ደርሰው አስጥለውታል፡፡
72′ ካርሎስ ዳምጠው ከፍፁም ቅጣት ምት የግራ ጠርዝ አክርሮ የመታው ኳስ ለጥቂት ወጥቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
71′ ማራኪ ወርቁ ወጥቶ ካርሎስ ዳምጠው ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
68′ ኤልያስ ማሞ ወጥቶ ጥላሁን ወልዴ ገብቷል፡፡
68′ ሳዲቅ ሴቾ ከግቡ በቅርብ ርቀት የሞከረውን ኳስ ጀማል በቀላሉ ይዞበታል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
63′ ታፈሰ ሰርካ ወጥቶ ሳሙኤል ታዬ ገብቷል፡፡
63′ ሳሙኤል ሳሊሶ ከቀኝ መስመር አክርሮ የመታውን ኳስ ሀሪሰን አውጥቶበታል፡፡
59′ በፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ያቡን ዊልያም አክርሮ በመምታት የሞከረውን ኳስ ተከላካዮች ተደርበው አውጥተውበታል፡፡
*** ከሁለቱም ወገን አንድ አንድ ተጫዋች በቀይ ካርድ በመውጣቱ በእኩል ቁጥር ጨዋታው እየተካሄደ ይገኛል፡፡
57′ በሃይሉ ግርማ ከርቀት የመታውን ኳስ ሀሪሰን በቀላሉ ይዞበታል፡፡
55′ መከላከያ የክስ ሪዘርቭ በማስያዝ ጨዋታው ቀጥሏል፡፡
ጎልልል!!!!
52′ ያቡን ዊልያም ከጀማል በተቃራኒ አቅጣጫ መትቶ አስቆጥሯል፡፡
ፍፁም ቅጣት ምት !
50′ በመከላከያ የግብ ክልል ቴድሮስ በቀለ በእጁ በመንካቱ የፍፁም ቅጣት ተሰጥቷል፡፡ ለተስፋዬ ቢጫ ለባዬ ገዛኸኝ የቀይ ካርድ ተሰጥቷል፡፡
ተጀመረ!
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
– – – – –
እረፍት!
የመጀመሪያው አጋማሽ ካለግብ ተጠናቋል፡፡
45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ደቂቃ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
ቢጫ ካርድ
39′ በሃይሉ ግርማ ኳስ በእጅ በመንካቱ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
38′ ኤልያስ ማሞ ከርቀት የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
ቀይ ካርድ
27′ ወንድይፍራው ጌታሁን በ2ኛ ቢጫ በአወዛጋቢ ሁኔታ ከሜዳ ወጥቷል፡፡
25′ ሳዲቅ ሴቾ ከግቡ የቀኝ መስመር በኩል ያገኘውን ኳስ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
22′ ንዳዬ ፋይስ (ጉዳት) ወጥቶ ሳዲቅ ሴቾ ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
20′ ነጂብ ሳኒ (ጉዳት) ወጥቶ ሙሉቀን ደሳለኝ ገብቷል፡፡
ቢጫ ካርድ
18′ ወንድይፍራው ጌታሁን በባዬ ገዛኸኝ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
12′ ባዬ ገዛኸኝ ከግብ ጠባቂው ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ የሞከረውን ኳስ ሀሪሰን ይዞበታል፡፡ የቡና ደጋፊዎች ባዬ ከጨዋታ ውጪ አቋቋም ላይ ነበር በሚል እየተቃወሙ ይገኛሉ፡፡
10′ ጨዋታው በተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ እስካሁን ምንም የግብ ሙከራ አልታየም፡፡
ተጀመረ
ጨዋታው በ1 ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተጀምሯል፡፡
– – – – – –
የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ
ሀሪሰን ሀሶው
አህመድ ረሺድ – ወንድይፍራው ጌታሁን – ኤፍሬም ወንድወሰን – አብዱልከሪም መሀመድ
አማኑኤል ዮሃንስ – ጋቶች ፓኖም – ኤልያስ ማሞ
ንዳዬ ፋይስ – ያቡን ዊልያም – እያሱ ታምሩ
የመከላከያ አሰላለፍ
ጀማል ጣሰው
ታፈሰ ሰርካ – አዲሱ ተስፋዬ – ቴዎድሮስ በቀለ – ነጂብ ሳኒ
ሚካኤል ደስታ – በሃይሉ ግርማ – ፍሬው ሰለሞን
ሳሙኤል ሳሊሶ – ባዬ ገዛኸኝ – ማራኪ ወርቁ