ካፍ ካይሮ በሚገኘው ዋና ፅህፈት ቤቱ የ2016 ኦሬንጅ ካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ የሶስተኛ ዙር ድልድል ዛሬ ይፋ ሆኗል፡፡ 16 ክለቦች ወደ ምድብ ድልድሉ ለመግባት የሚፋለሙ ሲሆን ከካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር ውጪ የሆኑት ስምንት ክለቦች ከኮንፌድሬሽን ካፕ ሁለተኛ ዙር ካለፉት ስምንት ክለቦች እርስበእርስ የሚጋጠሙ ይሆናል፡፡
በውድድሩ ላይ ብቸኛው የአልጄሪያ ተወካይ ሞሊዲያ ኦሎምፒክ ቤጃያ ከቱኒዚያው ሃያል ክለብ ኤስፔራንስ የሚያደርጉት የሰሜን አፍሪካ ደርቢ ከአሁኑ ትኩረትን ስቧል፡፡ የ2015 የካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ አሸናፊው ኤቷል ደ ሳህል ከጋቦኑ ሲኤፍ ሞናና ጋር ሲጋጠም የቻምፒየንስ ሊጉ አሸናፊ ቲፒ ማዜምቤ ከቱኒዚያው ስታደ ጋብሲየን ጋር ተደልድሏል፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ተወካዮቹ ኤል-ሜሪክ እና ያንግ አፍሪካንስ ከካውካብ ማራካሽ እና ከሳግራዳ ኤስፔራንስ ጋር ተደልድለዋል፡፡ የጋናው ሚዲአማ ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ፣ ፉስ ራባት ከስታደ ማሊያን እንዲሁም አሃሊ ትሪፖሊ ከምስር ኤል ማቃሳ ሌሎች ጨዋታዎች ናቸው፡፡
ከኮንፌድሬሽን ካፕ ሁለተኛ ዙር ያለፉ ክለቦች የመጀመሪያውን ጨዋታ ከሜዳ ውጪ ይጫወታሉ፡፡ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ከግንቦት 6-8 2016 ባሉት ቀናት ሲደረጉ የመልስ ጨዋታዎች ከግንቦት 17-18 2016 ይደረጋሉ፡፡
የሶስተኛ ዙር ጨዋታዎች፡
ሞሊዲያ ኦሎምፒክ ቤጃያ (አልጄሪያ) ከ ኤስፔራንስ ስፖርቲቭ ደ ቱኒዝ (ቱኒዚያ)
ስታደ ማሊያን (ማሊ) ከ ፋስ ዩኒየን ስፖርት ራባት (ሞሮኮ)
ኤቷል ስፖርቲቭ ደ ሳህል (ቱኒዚያ) ከ ሲኤፍ ሞናና (ጋቦን)
ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) ከ ስታደ ጋብሲየን (ቱኒዚያ)
አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) ከ ምስር ኤል ማቃሳ (ግብፅ)
ኤል ሜሪክ (ሱዳን) ከ ካውካብ አትሌቲክ ክለብ ማራካሽ (ሞሮኮ)
ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) ከ ሳግራዳ ኤስፔራንሳ (አንጎላ)
ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ) ከ ሚዲአማ (ጋና)