ፕሪሚየር ሊግ ፡ ዛሬ በተደረገ የ15ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ንግድ ባንክ ደደቢትን አሸንፏል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ዛሬ ተካሂዶ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደደቢትን 1-0 በመርታት ደረጃውን አሻሽሏል፡፡

ጥቂት የግብ ሙከራ እና ያልተደራጀ እንቅስቃሴ ባልታየበት የመጀመርያ አጋማሽ 17ኛው ደቂቃ ላይ በግራ መስመር ጠርዝ ላይ የታሪክ ጌትነት ስህተት ታክሎበት ያገኘውን ኳስ ፊሊፕ ዳውዚ በግሩም ሁኔታ ከመረብ አሳርፎ ንግድ ባንክን ለድል አብቅቷል፡፡ ያለፈው ሳምንት ጨዋታ በጉዳት ምክንያት ያልተጫወተው ፊሊፕ ግብ ከማስቆጠሩ በተጨማሪ በንግድ ባንክ የማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ ጉልህ ተጽእኖ ማበርከት ችሏል፡፡

የሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ከመጀመርያው በተሸለ የግብ ሙከራዎች እና የማጥቃት እቅስቃዎች የታዩ ቢሀንም ተጨማሪ ግብ ሳይቆጠር ጨዋታው በንግድ ባንክ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

የ15ኛ ሳምንት ውጤቶች

ኢትዮጵያ ቡና 1-0 መከላከያ
52′ ያቡን ዊልያም (ፍቅም)

ዳሽን ቢራ 4-0 ሀዲያ ሆሳዕና
22′ የተሻ ግዛው, 27′ 47′ 75′ ኤዶም ሆሶሮውቪ

ሀዋሳ ከተማ 2-0 ድሬዳዋ ከተማ
5′ አስቻለው ግርማ, 30′ ደስታ ዮሃንስ

ሲዳማ ቡና 0-1 ቅዱስ ጊዮርጊስ
36′ ሳላዲን ሰኢድ

አርባምንጭ ከተማ 0-0 ወላይታ ድቻ

ኤሌክትሪክ 0-1 አዳማ ከተማ 
57′ ታፈሰ ተስፋዬ

ደደቢት 0-1 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
17 ፊሊፕ ዳውዚ

የደረጃ ሰንጠረዥ

PicsArt_1461348740863

ከፍተኛ ግብ አግቢዎች ደረጃ

PicsArt_1461262717909

16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች

ማክሰኞ ሚያዝያ 18 ቀን 2008

09፡00 አዳማ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና (አዳማ)

09፡00 ወላይታ ድቻ ከ ዳሽን ቢራ (ቦዲቲ)

09፡00 ሀዲያ ሆሳዕና ከ ሀዋሳ ከተማ (ሆሳዕና)

09፡00 ድሬዳዋ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና (ድሬዳዋ)

11፡30 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኤሌክትሪክ (አአ ስታድየም)

ረቡዕ ሚያዝያ 19 ቀን 2008

09፡00 መከላከያ ከ ደደቢት (አአ ስታድየም)

11፡30 ኢትዮጵያ ንድ ባክ ከ አርባምንጭ ከተማ (አአ ስታድየም)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *