አዳማ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

አዳማ ከተማ 0-1 ኢትዮጵያ ቡና
64′ ያቡን ዊልያም

ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ደጋፊዎች በከፍተኛ ሁኔታ ደስታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
90′
አማኑኤል ዮሃንስ ወጥቶ ቶማስ እሸቱ ገብቷል፡፡

86′ ዮናታን ከበደ ነፃ የግብ ማስቆጠር አጋጣሚ አግኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አዳማ
75′
ሱሌማን መሃመድ ወጥቶ ሚካኤል ጆርጅ ገብቷል፡፡ ቅያሪው ለአዳማ የቅርፅ ለውጥ የሚያመጣ ይመስላል፡፡

ቢጫ ካርድ
75′
ሳላምላክ ተገኝ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
71′
ዊልያም ያቡን ወጥቶ አክሊሉ ዋለልኝ ገብቷል፡፡ ያቡን ግቡን ሲያስቆጥር ከግብ ጠባቂው ጋር በመጋጨቱ የተጎዳ ይመስላል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
69′
መስኡድ መሀመድ ወጥቶ ጥላሁን ወልዴ ገብቷል፡፡

ጎልልል!!!! ቡና
64′ ዊልያም ያቡን ከኤልያስ የተሻገረለትን ኳስ በመጠቀም የግብ ጠባቂውን መውጣተት ተመልክቶ በግሩም ሁኔታ አስቆጥሮ ቡናን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አዳማ ከተማ
59′
ጫላ ድሪባ ወጥቶ ዮናታን ከበደ ገብቷል፡፡

52′ ኤልያስ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ዊልያም በግንባሩ ሲገጨው ነጥሮ ለጥቂት አግዳሚውን ታኮ ወጥቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
49′
አህመድ ረሺድ በሱሌይማን ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ተጀመረ !!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል፡፡

picsart_1461655199502.jpg

– — –
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ ካለ ግብ ተጠናቋል፡፡

45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ደቂቃ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

ቢጫ ካርድ
44′
ብሩክ ቃልቦሬ ኤልያስ ላይ በሰራው ጥፋት የጨዋታውን የመጀመርያ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

43′ ጨዋታው በመሀል ሜዳ እንቅስቃሴ የተገደበ ሆኗል፡፡ ይህ ነው የሚባል ሙከራም እየተደረገ አይደለም፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አዳማ ከተማ
32′
ወንድሜነህ ዘሪሁን ወጥቶ ተስፋዬ ነጋሽ ገብቷል፡፡

25′ ዊልያም ከመሰመር ያሻገረውን ኳስ ኤልያስ 16:50 ላይ ሁለት ተጨዋቾችን አልፎ ግብ ለማስቆጠር የተመቸ ቦታ ላይ ቢገኝም በግቡ አናት ወደ ውጪ ሰዶታል፡፡

* * * ጨዋታው ከቆመበት ቀጥሏል፡፡

* * * በአሁኑ ሰአት ጨዋታው ተቋርጧል፡፡

15′ በጥላፎቅ ደጋፊዎች ጣራ ላይ ለመውጣት በመሞከር ላይ በመሆናቸው የጨዋታው ኮሚሽነር አደጋ እንዳይደርስ በሚል ጨዋታው እንዲቋረጥ አዘዋል፡፡

13′ በመጀመርያዎቹ 15 ደቂቃዎች ማራኪ ፉክክር እና የዳኛ ፊሽካ ያለበዛበት ወጥ እንቅስቃሴ እየተመለከትን እንገኛለን፡፡

6′ የኤፍሬምና የሀሪሰንን አለመግባባት ተከትሎ ታከለ ያገኘውን ኳስ ሀሪሰንን አልፎ በአስገራማሚ ሁኔታ ስቶታል፡፡

3′ ዊልያም ከመስመር ሰብሮ በመግባት ለእያሱ ሰጥቶት እያሱ አገባው ሲባል ጃፋር አወጣበት፡፡ የሚያስቆጭ አጋጣሚ!!!

ተጀመረ!!!
ጨዋታው 09:03 ሲል ተጀመረ፡፡

image

08:50 ሁለቱም ቡድኖች ወደ መልበሻ ክፍል ተመልሰዋል፡፡

08:35 የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች በማሟሟቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

08:30 እጅግ በርካታ የቡና ደጋፊና በርካታ የስፖርት አፍቃሪ እንዲሁም የአዳማ ከተማ ደጋፊዎች የአዳማን አበበ በቂላ ስቴዲዮም አድምቀውታል
– – –

የአዳማ ከተማ አሰላለፍ
ጃፈር ደሊል
ሞገስ ታደሰ – ተስፈዬ በቀለ – ምንተስኖት ከበደ – ሱሌማን መሃመድ
ብሩክ ቃልቦሬ – ፋሲካ አስፋው – ወድሜነህ ዘሪሁን
ታከለ አለማየሁ – ታፈሰ ተስፋዬ – ጫላ ድሪባ

የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ
ሀሪሰን ሄሶው
አህመድ ረሺድ – ኢኮ ፊቨ – ኤፍሬም ወንድወሰን – ሳላምላክ ተገኝ
አብዱልከሪም መሃመድ – ኤልያስ ማሞ – መስኡድ መሃመድ
አማኑኤል ዮሃንስ – ያቡን ዊልያም – እያሱ ታምሩ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *