የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ዛሬ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች አስተናግዶ ደቡብ ፖሊስ ያልተጠበቀ ድል ሲያስመዘግብ አክሱም ከ ሙገር ካለ ግብ ተለያይተዋል፡፡
ሀዋሳ ላይ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አአ ከተማን ያስተናገደው ደቡብ ፖሊስ 4-0 አሸንፏል፡፡ የደቡብ ፖሊስን የድል ግቦች ወንድሜነህ አይናለም ፣ ሚካኤል ለማ ፣ ዘላለም እና ወንድይፍራው አስቆጥረዋል፡፡ ከመጥፎ አጀማመር በኀላ እያንሰራራ የሚገኘው ደቡብ ፖሊስ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ብቻ 12 ግቦች ተጋጣሚዎቹ ላይ አስቆጥሯል፡፡
ወደ አክሱም የተጓዘው ሙገር ሲሚንቶ ከአክሱም ከተማ ጋር ካለ ግብ ተለያይቷል፡፡
የተስተካካይ ጨዋታዎች ውጤቶች እና ቀጣይ ተስተካካይ ጨዋታዎች
አርብ ሚያዝያ 14 ቀን 2008
ነቀምት ከተማ 0-0 ነገሌቦረና (ነቀምት)
(የ8ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ)
13ኛ ሳምንት
ማክሰኞ ሚያዝያ 18 ቀን 2008
ደቡብ ፖሊስ 4-0 አአ ከተማ (ሀዋሳ)
አክሱም ከተማ 0-0 ሙገር ሲሚንቶ (አክሱም)
ረቡዕ ሚያዝያ 19 ቀን 2008
ነገሌ ቦረና ከ ጅማ አባ ቡና (ነገሌ ቦረና)
14ኛ ሳምንት
እሁድ ሚያዝያ 23 ቀን 2008
09:00 ሻሸመኔ ከተማ ከ አአ ከተማ (ሻሸመኔ)
09:00 ሙገር ሲሚንቶ ከ ባህርዳር ከተማ (መድን ሜዳ)
እሁድ ሚያዝያ 30 ቀን 2008
09:00 ጅማ አባ ቡና ከ አአ ዩኒቨርሲቲ (ጅማ)
15ኛ ሳምንት
ማክሰኞ ሚያዝያ 25 ቀን 2008
09:00 አርሲ ነገሌ ከ ጅማ አባ ቡና (አርሲ ነገሌ)
አርብ ሚያዝያ 28 ቀን 2008
09:00 አአ ከተማ ከ ነቀምት ከተማ (አበበ ቢቂላ)
09:00 ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ከ ሙገር ሲሚንቶ (ደብረብርሃን)