ፕሪሚየር ሊግ ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነቱን ሲያጠናክር ቡና ደረጃውን ማሻሻሉን ቀጥሏል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት 5 ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደው ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነቱን ያጠናከረበትን ድል አስመዝግቧል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና 3ኛ ተከታታይ ድሉን ሲያሳካ የድሬዳዋ ከተማ ከሲዳማ ቡና ያደረጉት ጨዋታ በከባድ ዝናብ ምክንያት ተቋርጧል፡፡

አዳማ
09:00 ላይ ኢትዮጵያ ቡናን ያስተናገደው አዳማ ከተማ 1-0 ተሸንፎ ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ያለውን ልዩነት ለማስፋት ተገዷል፡፡ ሞቅ ያለ ድባብ እና ድንቅ የመጀመርያ አጋማሽ እንቅስቃሴ በታየበት ጨዋታ በ64ኛው ደቂቃ የቡናን የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈው ያቡን ዊልያም ነው፡፡ ኢትዮጵያ ቡና በሁለተኛው ዙር ያደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች በያቡን ዊልያም ብቸኛ ግቦች ታግዞ በተመሳሳይ 1-0 በማሸነፍ ደረጃውን በከፍተኛ ሁኔታ ማሻሻል ችሏል፡፡

PicsArt_1461693470197

ቦዲቲ
09:00 ላይ ወላይታ ድቻ ዳሽን ቢራን አስተናግዶ ካለግብ አቻ ተለያይቷል፡፡ ወላይታ ድቻ በተከታታይ ያደረጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች ካለግብ በአቻ ውጤት በመፈፀም ደረጃውን ማሻሻል ሳይችል ቀርቷል፡፡

ሆሳዕና
09:00 ላይ ሀዲያ ሆሳዕና ሀዋሳ ከተማን አስተናግዶ አቻ ተለያይቷል፡፡  ሀዋሳ ከተማ በደስታ ዮሃንስ የ3ኛ ደቂቃ ጎል ቀዳሚ መሆን ቢችልም ከግማሽ የውድድር ዘመን ሆሳዕናን የተቀላቀለው ተመስገን ገብረፃዲቅ በቀድሞ ክለቡ ላይ አስቆጥሮ ባለሜዳዎቹን አቻ አድርጓል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ወደ መልሻ ክፍል ያመሩት በቢንያም ገመቹ የ27ኛ ደቂቃ ጎል በሃዲያ ሆሳዕና መሪነት ነበር፡፡ ከእረፍት መልስ በ69ኛው ደቂቃ አስቻለው ግርማ ለሀዋሳ ከተማ አስቆጥሮ ጨዋታው በአቻ ውጤት ተፈፅሟል፡፡

ድሬዳዋ
09:00 ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና ያደረጉት ጨዋታ እስከ መጀመርያው አጋማሽ ድረስ በዝናብ ታጅቦ ተካሂዶ የሁለተኛው አጋማሽ ሳይጀመር እንዲቋረጥ ተደርጎ ነገ 4፡00 ላይ ከቆመበት እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡ ጨዋታው እስኪቋረጥ ድረስ ግብ አልተቆጠረም፡፡
image

አዲስ አበባ
11፡30 ላይ በተደረገው ብቸኛ ጨዋታ የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኤሌክትሪክን በቀላሉ 3-0 አሸንፎ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡ በፈጣን እንቅስቀሴ በተጀመረው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጀመርያዎቹ 30 ደቂቃዎች ባስቆጠራቸው ግቦች ታግዞ አሸንፏል፡፡ በ14ኛው ደቂቃ አዳነ ግርማ ከመስር የተሸገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ፈረሰኞቹን ቀዳሚ ሲያደርግ አይዛክ ኢዜንዴ ከቅጣት ምት ሁለተኛውን በሃይሉ አሰፋ ደግሞ ሶስተኛውን ግብ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

የደረጃ ሰንጠረዥ
image

የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ደረጃ
image

ነገ
የ16ኛ ሳምንት ቀሪ 2 ጨዋታዎች ነገ በአአ ስታድየም ሲደረጉ 09:00 ላይ መከላከያ ከ ደደቢት ፣ 11:30 ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ከ አርባምንጭ ከተማ ይጫወታሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *