የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል፡፡ ዛሬ ወደ ነገሌ ቦረና የተጓዘው ጅማ አባ ቡና 3-1 በማሸነፍ ከተከታዩ አአ ከተማ ያለውን ርቀት ወደ 4 ከፍ አድርጓል፡፡
ለጅማ አባ ቡና የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች አጥቂ የሆነው አሜ መሃመድ 2 ግቦች ሲያስቆጥር ኪዳኔ አሰፋ አንድ አስቆጥሯል፡፡ ለነገሌ ቦረና ደግሞ ዳግም በቀለ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡
የተስተካካይ ጨዋታዎች ውጤቶች እና ቀጣይ ተስተካካይ ጨዋታዎች
አርብ ሚያዝያ 14 ቀን 2008
ነቀምት ከተማ 0-0 ነገሌቦረና (ነቀምት)
(የ8ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ)
13ኛ ሳምንት
ማክሰኞ ሚያዝያ 18 ቀን 2008
ደቡብ ፖሊስ 4-0 አአ ከተማ (ሀዋሳ)
አክሱም ከተማ 0-0 ሙገር ሲሚንቶ (አክሱም)
ረቡዕ ሚያዝያ 19 ቀን 2008
ነገሌ ቦረና 1-3 ጅማ አባ ቡና (ነገሌ ቦረና)
14ኛ ሳምንት
እሁድ ሚያዝያ 23 ቀን 2008
09:00 ሻሸመኔ ከተማ ከ አአ ከተማ (ሻሸመኔ)
09:00 ሙገር ሲሚንቶ ከ ባህርዳር ከተማ (መድን ሜዳ)
እሁድ ሚያዝያ 30 ቀን 2008
09:00 ጅማ አባ ቡና ከ አአ ዩኒቨርሲቲ (ጅማ)
15ኛ ሳምንት
ማክሰኞ ሚያዝያ 25 ቀን 2008
09:00 አርሲ ነገሌ ከ ጅማ አባ ቡና (አርሲ ነገሌ)
አርብ ሚያዝያ 28 ቀን 2008
09:00 አአ ከተማ ከ ነቀምት ከተማ (አበበ ቢቂላ)
09:00 ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ከ ሙገር ሲሚንቶ (ደብረብርሃን)