በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ ተዋረድ የሚመራው የቴክኒክ ኮሚቴ መሰናበቱን ለፌዴሬሽኑ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሶከር ኢትዮዽያ ገልፀዋል፡፡
የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሆኑት በአቶ ዘሪሁን ቀቀቦ የሚመራው ይህ ኮሚቴ ዶክተር ሲራክ ፣ አቶ ሰለሞን አባተ ፣ አቶ አበራ እና ሌሎችም አባላት ይገኙበታል፡፡ ኮሚቴው በተለያየ ጊዜ ግምገማዎችን ያቀርብ የነበረ ሲሆን እደወትሮው ሁሉ የአሰልጣኝ ዮሐንስን የግምገማ እና ስንብት ሪፖርት ባቀረቡበት ቅፅበት መሰናበታቸው ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል ከ15 ቀን በኋላ በሚኖረው የስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ በመኮንን ኩሩ የሚመራው የቴክኒክ ዲፓርትመንቱ እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አንዳንድ ምንጮችም ዲፓርትመንቱ ፈርሶ አንደአዲስ መዋቀሩ እንደማይቀር ተናግረዋል፡፡