ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ፡ በዛሬ ጨዋታዎች ደደቢት እና ንግድ ባንክ ድል ቀንቷቸዋል

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ መካከለኛ-ሰሜን ዞን 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም 9፡00 እና 11፡00 ቀጥለው ሲከናወኑ ደደቢት እና ንግድ ባንክ ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በደረጃ ሰንጠረዡ አናት እና ግርጌ ላይ የሚገኙት ደደቢት እና እቴጌን ያገናኘው ጨዋታ ስድስት ጎሎች ተስተናግደውበታል፡፡

ጥሩ የጨዋታ ፉክክር በተስተዋለበት የመጀመርያው አጋማሽ ደደቢቶች በርካታ ጎሎችን ያስቆጥራሉ ተብሎ ቢጠበቅም የመጀመሪያው አጋማሽ ግን 0-0 በሆነ ውጤት ነበር የተጠናቀቀው፡፡

ከእረፍት መልስ ተጠናክረው የገቡት ደደቢቶች በሎዛ አበራ እና መስከረም ካንኮ ሁለት እንዲሁም በኤደን ሽፈራው ሰናይት ባሩዳ አንድ አንድ ጎሎች እቴጌን ማሸነፍ ችለዋል፡፡

11፡00 ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ቅድስተ ማሪያም ዩንቨርስቲን ያገናኘው ጨዋታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ወለላ ቡልቻ ቅድስተ ማርያም ለ8 ደቂቃዎች ብቻ መሪ የሆነበትን ግብ ስታስቆጥር ከስምንት ደቂቃዎች በኃላ ባንክ የቅድስተ ማርያም ተከላካዮች በሰሩት ጥፋት ያገኙትን የፍፁም ቅጣት ምት በህይወት ደንጊሶ አማካይነት ወደ ግብነት በመቀየር አቻ መሆን ችለዋል፡፡

ከእረፍት መልስ እንደ መጀመሪያ አጋማሹ ሁሉ የቅድስተ ማሪያም ተከላካይ ኳስ በእጁዋ በመንካቷ ምክንያት የተገኘውን ሁለተኛ የፍጹም ቅጣት ምት ተቀይራ የገባችው ሽታዩ ሲሳይ ማስቆጠር ችላለች፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁነኛ አጥቂ ሽታዬ ሲሳይ ተቀይራ ከገባችበት ጊዜ ጀምሮ ጥሩ እንቅስቃሴዎችን ያደረገች ሲሆን የቡድኑዋን የማሳረግያ ግብ ከቅጣት ምት በማስቆጠር የጨዋታው ውጤት 3-1 እንዲሆን አስችላለች፡፡

በዚሁ በ14ኛ ሳምንት ትላንት ሁለት ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ በትዕግስት ዘውዴ እና ማህደር ጀማነህ ግቦች ሙገር ሲሚንቶን 2-0 በመርታት 3ኛ ደረጃውን አስጠብቋል፡፡

09:00 ላይ ዳሽን ቢራን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና 5-0 ተሸንፏል፡፡ የጎንደሩን ክለብ ግቦች ሩት ያደታ ፣ ጥሩወርቅ ወዳጄ ፣ ሄለን እሸቱ ፣ አሳቤ ሙሶ እና እየሩሳሌም ተሾመ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ነገ የ14ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ሲደረግ 10:00 ላይ ኤሌክትሪክ ከ መከላከያ ይፋለማሉ፡፡

 

የደረጃ ሰንጠረዥ

PicsArt_1461956917299

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *