በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ዛሬ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ሻሸመኔ ላይ ተካሂዶ አአ ከተማ ሻሸመኔን 2-1 በመርታት ወደ አሸናፊነት ተመልሷል፡፡
በዝናብ የጨቀየ ሜዳ ላይ በተደረገው ጨዋታ በተጨማሪ ሰአት ሁለት ግቦች ተቆጥረዋል፡፡
አአ ከተማ በምንያምር ጴጥሮስ ግብ 1-0 ሲመራ ቆይቶ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሊጠናቀቅ 3 ደቂቃ ሲቀረው ሙህዲን አብደላ ሻሸመኔን በፍጹም ቅጣት ምት አቻ አድርጓል፡፡ ጨዋታው በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ አአ ከተማዎች ያገኙትን የፍጹም ቅጣት ምት በሃይለየሱስ መልካ አማካኝነት አስቆጥረው አሸንፈዋል፡፡
የተስተካካይ ጨዋታዎች ውጤቶች እና ቀጣይ ተስተካካይ ጨዋታዎች
አርብ ሚያዝያ 14 ቀን 2008
ነቀምት ከተማ 0-0 ነገሌቦረና (ነቀምት)
(የ8ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ)
13ኛ ሳምንት
ማክሰኞ ሚያዝያ 18 ቀን 2008
ደቡብ ፖሊስ 4-0 አአ ከተማ (ሀዋሳ)
አክሱም ከተማ 0-0 ሙገር ሲሚንቶ (አክሱም)
ረቡዕ ሚያዝያ 19 ቀን 2008
ነገሌ ቦረና 1-3 ጅማ አባ ቡና (ነገሌ ቦረና)
14ኛ ሳምንት
ቅዳሜ ሚያዝያ 22 ቀን 2008
ሙገር ሲሚንቶ 0-1 ባህርዳር ከተማ (መድን ሜዳ)
እሁድ ሚያዝያ 23 ቀን 2008
ሻሸመኔ ከተማ 1-2 አአ ከተማ (ሻሸመኔ)
እሁድ ሚያዝያ 30 ቀን 2008
09:00 ጅማ አባ ቡና ከ አአ ዩኒቨርሲቲ (ጅማ)
15ኛ ሳምንት
ማክሰኞ ሚያዝያ 25 ቀን 2008
09:00 አርሲ ነገሌ ከ ጅማ አባ ቡና (አርሲ ነገሌ)
አርብ ሚያዝያ 28 ቀን 2008
09:00 አአ ከተማ ከ ነቀምት ከተማ (አበበ ቢቂላ)
09:00 ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ከ ሙገር ሲሚንቶ (ደብረብርሃን)