የኢትዮጵያ U-20 ብሄራዊ ቡድን ከጋና ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጅቱን በዚህ ወር መጨረሻ ይጀምራል

ከ20 አመት በታች የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ከጋና ጋር ላለበት የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች የማጣርያ ጨዋታ ዝግጅት በዚህ ወር መጨረሻ ለተጫዋቾቹ ጥሪ በማድረግ እንደሚጀምር ታውቋል፡፡

የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ግርማ ሃብተዮሃንስ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት ለጋናው ጨዋታ ጠንካራ ዝግጅት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

” ስለ ጋና ብሔራዊ ቡድን መረጃ ለማግኘት ጥረት ማድረግ ጀምረናል፡፡ በዝግጅታችን በሶማልያው ጨዋታ የነበሩብን ድክመቶች አስተካክለን ለመቅረብ እንሰራለን፡፡ ቡድናችን ላይ ከፍተኛ መሻሻል አይቼበታለው፡፡ ለጋናውም ጨዋታ ጥሩ ዝግጅት እናደርጋለን፡፡ ” ያሉት አሰልጣኝ ግርማ በሶማልያው የደርሶ መልስ ጨዋታ የነበሩት ተጫዋቾች ላይ ጥቂት ተጫዋቾች ተጨምረው ዝግጅት እንደሚጀምሩ ገልፀዋል፡፡

” ብዙ የሚቀነሱ ተጫዋቾች ባይኖሩም የሚጠሩ አዲስ ተጨዋቾች ግን ይኖራሉ፡፡ በከፍተኛ ሊግ ክለቦች ውስጥ የሚገኙት ተጫዋቾች ለክለቦቻቸው አገልግሎት ሰጥተው እስኪመጡ የዝግጅቱ የተወሰኑ ቀናት ላይ አይኖሩም፡፡ ሌሎቹ ተጫዋቾች ግን በጥሪው ቀን መሰረት አብረውን ዝግጅት ይጀምራሉ ” ብለዋል፡፡

PicsArt_1462189928599

ካፍ ባወጣው የማጣሪያ ጨዋታዎች ፕሮግራም መሰረት የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከጋና ጋር የሚያደርገውን የመጀመርያ ጨዋታ ግንቦት 14 ቀን 2008 አዲስ አበባ ላይ ያካሄዳል፡፡ የመልሱ ግጥሚያ ደግሞ ከሰኔ 3 እስከ 5 ቀን 2008 ባሉት ቀናት ጋና በምትመርጠው ከተማ እንደሚከናወን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *