ፕሪሚየር ሊግ፡ ትላንት ከተቋረጠበት በቀጠለው ጨዋታ ሲዳማ ቡና ሀዲያ ሆሳዕናን አሸንፎ ደረጃውን አሻሽሏል

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ትላንት እየተካሄደ የነበረው የሲዳማ ቡና እና ሀዲያ ሆሳዕና ጨዋታ በጣለው ከባድ ዝናብ 21ኛው ደቂቃ ላይ መቋረጡ የሚታወስ ነው፡፡ ጨዋታው ዛሬ 4፡00 ላይ ከቆመበት እንዲቀጥል በተወሰነው መሰረት በቀጠለው ጨዋታ ሲዳማ ቡና 1-0 አሸንፎ ደረጃውን አሻሽሏል፡፡

ሲዳማ ቡና የጨዋታውን ብቸኛ የማሸነፍያ ግብ ያገኘው ጨዋታው በተጀመረ በ5ኛው ደቂቃ (26ኛ ደቂቃ) ከማዕዘን የተሸገረው ኳስ ሳውሬል ኦልሪሽ ባስቆጠራት ግብ ነው፡፡ ከፍተኛ ውጥረት እና በርካታ ካርዶች በተመዘዙበት ጨዋታ ተሸናፊዎቹ ሀዲያ ሆሳዕናዎች በከፍተኛ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ሜዳውን ለቀው ወጥተዋል፡፡

ሀዲያ ሆሳዕና በሁለተኛው ዙር በርካታ የፕሪሚየር ሊግ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን በማስፈረሙ ከመውረድ ስጋት ለመትረፍ ያግዘዋል ቢባልም እንደተጠበቀው ሳይሆን ቀርቶ የደረጃ ሰንጠረዡን ግረጌ እንደያዘ ቀጥሏል፡፡

የ17ኛ ሳምንት ውጤቶች

ድሬዳዋ ከተማ 1-0 ቅዱስ ጊዮርጊስ (ድሬዳዋ)
76′ ዳዊት እስጢፋኖስ

ሲዳማ ቡና 1-0 ሀዲያ ሆሳዕና (ይርጋለም)
26′ ሳውሬል ኦልሪሽ

ሀዋሳ ከተማ 0-0 ወላይታ ድቻ (ሀዋሳ)

ዳሽን ቢራ 0-0 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (ጎንደር)

ደደቢት 1-0 አዳማ ከተማ (አአ ስታድየም)
46′ ዳዊት ፍቃዱ

አርባምንጭ ከተማ 0-0 መከላከያ (አርባምንጭ)

ኢትዮጵያ ቡና -0 ኤሌክትሪክ (አአ ስታድየም) 
59′ ጋቶች ፓኖም (ፍቅም)
 

የደረጃ ሰንጠረዥ

image
 

የ18ኛ ሳምንት ጨዋታዎች

ቅዳሜ ሚያዝያ 29 ቀን 2008

10፡00 ኤሌክትሪክ ከ ደደቢት (አአ ስታድየም)

እሁድ ሚያዝያ 30 ቀን 2008

09፡00 አዳማ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ (አዳማ)

09፡00 ወላይታ ድቻ ከ ሲዳማ ቡና (ቦዲቲ)

09፡00 ሀዲያ ሆሳዕና ከ ድሬዳዋ ከተማ (ሆሳዕና)

10፡00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና (አአ ስታድየም)

ሰኞ ግንቦት 1 ቀን 2008

09፡00 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ሀዋሳ ከተማ (አአ ስታድየም)

11፡30 መከላከያ ከ ዳሽን ቢራ (አአ ስታድየም)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *