የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መካከለኛ – ሰሜን ዞን 15ኛ ሳምንት ትላንት እና ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ቀጥሏል፡፡
ትላንት በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ቅድስት ማርያም እቴጌን 2-1 ሲያሸንፍ መከላከያ ኢትዮጵያ ቡናን 6-0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡
ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኤሌክትሪክን 4-0 በመርታት ከደደቢት ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 5 አጥብቧል፡፡ ቀጥሎ በተካሄደው የደደቢት እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸንፏል፡፡ ደደቢት በሎዛ አበራ ግብ ቀዳሚ መሆን ቢችልም ትዕግስት ዘውዴ እና ትመር ጠንክር ያስቆጠሯቸው ግቦች የደደቢትን የውድድር ዘመኑ 100% ጉዞ አሰናክሎታል፡፡
የሊጉ 14ኛ ሳምንት ነገ በሚደረግ ጨዋታ ሲጠናቀቅ ሙገር ሲሚንቶ ከልደታ ክ/ከተማ ይጫወታሉ፡፡ ዳሽን ቢራ ደግሞ በዚህ ሳምንት አራፊ ቡድን ነው፡፡
የ14ኛ ሳምንት ውጤቶች
ረቡዕ ሚያዝያ 26 ቀን 2008
ቅድስት ማርያም 2-1 እቴጌ
መከላከያ 6-0 ኢትዮጵያ ቡና
ሀሙስ ሚያዝያ 27 ቀን 2008
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 4-0 ኤሌክትሪክ
ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-1 ደደቢት
አርብ ሚያዝያ 28 ቀን 2008
ሙገር ሲሚንቶ ከ ልደታ
የደረጃ ሰንጠረዥ