የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች ወደ መገባደጃቸው ተቃርበዋል፡፡ ዛሬ ሊካሄዱ ከታቀደላቸው ሁለት ጨዋታዎችም አንዱ ተካሂዶ አአ ከተማ በድል የመጀመርያውን ዙር አጠናቋል፡፡ የሰሜን ሸዋ እና ሙገር ሲሚንቶ ጨዋታ ደግሞ በዝናብ ምክንያት ለእሁድ ተላልፏል፡፡
በ9፡00 አበበ ቢቂላ ላይ ነቀምት ከተማን ያስተናገደው አአ ከተማ 1-0 በማሸነፍ ከጅማ አባ ቡና ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት መልሶ አጥብቧል፡፡ የአአ ከተማን የድል ግብ በመጀመርያው አጋማሽ ከመረብ ያሳረፈው ፍፁም ካርታ ነው፡፡
አአ ከተማ በጨዋታው የነበረውን ከፍተኛ የጨዋታ ብልጫ እና በርካታ የግብ እድሎች መጠቀም ቢችል ውጤቱ ከዚህም በላቀ የሚሰፋበት እድል የነበረ ሲሆን የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ኮከብ ዮናታን ብርሃነ በጨዋታው ያሳየው እንቅስቃሴ ከተመልካች አድናቆት ተችሮታል፡፡
በምድብ ሀ በሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን እና ሙገር ሲሚንቶ መካከል ዛሬ ሊደረግ የታሰበው ጨዋታ በደብረብርሃን ባለው ዝናባማ የአየር ንብረት ምክንያት ወደ እሁድ ሚያዝያ 30 ተሸጋግሯል፡፡
የደረጃ ሰንጠረዥ
የተስተካካይ ጨዋታዎች ውጤቶች እና ቀጣይ ተስተካካይ ጨዋታዎች
አርብ ሚያዝያ 14 ቀን 2008
ነቀምት ከተማ 0-0 ነገሌቦረና (ነቀምት)
(የ8ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ)
13ኛ ሳምንት
ማክሰኞ ሚያዝያ 18 ቀን 2008
ደቡብ ፖሊስ 4-0 አአ ከተማ (ሀዋሳ)
አክሱም ከተማ 0-0 ሙገር ሲሚንቶ (አክሱም)
ረቡዕ ሚያዝያ 19 ቀን 2008
ነገሌ ቦረና 1-3 ጅማ አባ ቡና (ነገሌ ቦረና)
14ኛ ሳምንት
ቅዳሜ ሚያዝያ 22 ቀን 2008
ሙገር ሲሚንቶ 0-1 ባህርዳር ከተማ (መድን ሜዳ)
እሁድ ሚያዝያ 23 ቀን 2008
ሻሸመኔ ከተማ 1-2 አአ ከተማ (ሻሸመኔ)
እሁድ ሚያዝያ 30 ቀን 2008
09:00 ጅማ አባ ቡና ከ አአ ዩኒቨርሲቲ (ጅማ)
15ኛ ሳምንት
ማክሰኞ ሚያዝያ 25 ቀን 2008
አርሲ ነገሌ 0-2 ጅማ አባ ቡና (አርሲ ነገሌ)
አርብ ሚያዝያ 28 ቀን 2008
አአ ከተማ 1-0 ነቀምት ከተማ (አበበ ቢቂላ)
እሁድ ሚያዝያ 30 ቀን 2008
09:00 ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ከ ሙገር ሲሚንቶ (ደብረብርሃን)