ዜና እረፍት፡ የሀዋሳ ከተማው ግብ ጠባቂ ክብረአብ ዳዊት በእሳት አደጋ ህይወቱ አለፈ

የሀዋሳ ከተማው ግብ ጠባቂ ክብረአብ ዳዊት ትላንት ለሊት በመኖርያ ቤቱ በተነሳ የእሳት አደጋ ህይወቱ በአሳዛኝ ሁኔታ አልፏል፡፡

ክብረአብ ከ3 አመት ሴት እና የወራት እድሜ ካለው ወንድ ልጁ ጋር በተኛበት በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ነበር ህይወቱ ያለፈችው፡፡ በአደጋው የክብረአብ ሁለቱም ልጆቹ ህይወት ጭምር ሲያልፍ ባለቤቱ ከእሳት አዳገው ተርፋለች፡፡

የክብረአብ እና ልጆቹ አስከሬን በአሁኑ ሰአት ለምርመራ በሆስፒታል የሚገኝ ሲሆን በአካባቢው የተቃጠለው የክብረአብ መኖርያ ቤት ብቻ እንደሆነና ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ የቀብር ስነስርአቱም ነገ ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ክብረአብ ዳዊት በሀዋሳ ከተማ ከ2007 ጀምሮ በተጠባባቂ ግብ ጠባቂነት እየተጫወተ የነበረ ሲሆን በ2007 በማርያኖ ባሬቶ በሚመራው የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ተካትቶ ሱዳንን በገጠመው ቡድን ቋሚ ተሰላፊ ነበር፡፡

ሶከር ኢትዮጵያ በክብረአብ እና ልጆቹ ድንገተኛ እና ልብ የሚሰብር እረፍት የተረሰማትን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀች ለቤተሰቦቹ ፣ ለወዳጅ ዘመዶ እንዲሁም ለስፖርት ቤተሰቡ መጽናናትን ትመኛለች፡፡

6 thoughts on “ዜና እረፍት፡ የሀዋሳ ከተማው ግብ ጠባቂ ክብረአብ ዳዊት በእሳት አደጋ ህይወቱ አለፈ

Leave a Reply

error: