ደደቢት ከ ጅማ አባ ቡና | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FT   ደደቢት   1-1  ጅማ አባ ቡና  

–  88′ ጌታነህ ከበደ |  27‘ መሀመድ ናስር 


ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

90+2′ ጅማዎች የሞከሩትን ኳስ ክሌመንት ሲይዘው ኳሷ ከግቧ መስመር አልፋ ነበር በሚል አባ ቡናዎች ቅሬታቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

ጎልልል!!! ደደቢት
88′ ጌታነህ ከበደ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮ ደደቢትን አቻ አድርጓል፡፡

ቢጫ ካርድ
84′ ኄኖክ ካሳሁን በሮበን ኦባማ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ጅማ አባ ቡና
78′ ሀይደር ሸረፋ ወጥቶ ልደቱ ጌታቸው ገብቷል፡፡

75′ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ ኩሊባሊ በግንባሩ በመግጨት ሞክሮ ጀማል አውጥቶበታል፡፡

70′ አሜ የክሌመንትን መውጣች ተመልክቶ የሞከረው ኳስ ኢላማውን ሳይጠብቅ ቀርቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
65′ ሰለሞን ሐብቴ ወጥቶ ሮበን ኦባማ ገብቷል፡፡

ቀይ ካርድ!
63′ መሀመድ ናስር በካድር ኩሊባሊ ላየይ በሰራው ጥፋት በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ጅማ አባ ቡና
60′ ዳዊት ተፈራ ወጥቶ ክሪዚስቶም ንታምቢ ገብቷል

56′ አሜ መሀመድ ከማዕዘን የተሻማውን ኳስ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

53′ ኤፍሬም አሻሞ ከተከላካዮች አምልጦ የሞከረው ኳሰ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

52′ የሁለተኛው አጋማሽ እንደመጀመርያው መሆን አልቻለም፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

የእረፍት ሰአት የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት 
አቤል እንዳለ ወጥቶ ስዩም ተስፋዬ ገብቷል፡፡

እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ በጅማ አባ ቡና መሪነት ተጠናቋል፡

የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
42′ አይናለም ኃይለ ወጥቶ ብርሀሃኑ ቦጋለ ገብቷል፡፡

40′ ጨዋታው ፈጣን እነቅስቀቃሴ ቢታይበትም በሚቆራረጡ ኳሶች እነና በዳኛው ተደጋጋሚ ፊሽካ አሰልቺ ገፅታን እየተላበሰ ይገኛል፡፡

* መሀመድ ናስር በጅማ አባ ቡና ማልያ የመጀመርያ ግቡን አስቆጥሯል፡፡


ጎልልል!!!! ጅማ አባ ቡና !!!!
27′ መሀመድ ናስር በደደቢት የመሀል ተከላካዮች መሀል ሆነኖ የግብ ጠባቂውን አቋቋም ተመልክቶ ግሩም ጎል አስቆጥሯል፡

የተጫዋች ለውጥ – ጅማ አባ ቡና
25′
ሲሳይ ባንጫ በጉዳት ወጥቶ ጀማል ጣሰው ገብቷል፡፡ ጀማል ከ2 ወራት ጉዳት በኋላ ወደ ሜዳ ተመልሶ ጨዋታ ለማድረግ ወደ ሜደዳ ገብቷል፡፡

21′ አቤል እንዳለ የአባ ቡና ተከላካዮችን መዘናጋት ተከትሎ ይዞ የገባውን ኳስ ወደ ግብ ከመሞከሩ በፊት ሲሳይ ደርሶ አድኖበታል፡፡

14′ ጌታነህ ከበደ በጥሩ ሁኔታ ወደ ሳጥን ገብቶ አገባው ተብሎ ሲጠበቅ ቢያድግልኝ ኤልያስ አስጥሎታል፡፡

12′ ሰለሞን ሐብቴ ከርቀት የሞከረውን ኳስ ሲሳይ ባንጫ አድኖበታል፡፡

10′ በጥሩ ቅብብል ኄኖክ ኢሳይያስ ያሻገረውን ኳስ ክሌመንት ቀድሞ አውጥቶበታል፡፡ የተመለሰውን ኳስ ዳዊት ተፈራ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡ ጅማ አባ ቡና በመጀመርያዎቹ 10 ደቂቃዎች የተሻለ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

የመጀመርያ ሙከራ!
7′ 
አሜ መሀመድ ወደ መሀል በመግባት ለዳዊት ያመቻቸለትን ኳስ ዳዊት ከሳጥን ውጪ ሞክሮ በግቡ ቋሚ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በጅማ አባ ቡናው መሀመድ ናስር አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

የደደቢት አሰላለፍ

33 ክሌመንት አዞንቶ

15 ደስታ ደሙ – 14 አክሊሉ አየነው – 6 አይናለም ኃይለ – 16 ሰለሞን ሐብቴ

24 ካድር ኩሊባሊ – 18 አቤል እንዳለ

19 ሽመክት ጉግሳ – 8 ሳምሶን ጥላሁን – 21 ኤፍሬም አሻሞ 

9 ጌታነህ ከበደ


ተጠባባቂዎች

22 ታሪክ ጌትነት 

7 ስዩም ተስፋዬ

10 ብርሃኑ ቦጋለ

12 ሮበን ኦባማ

25 ብርሃኑ አሻሞ

35 አኩዌር ቻም

29 ኤሪክ ኦፖኩ


የጅማ አባ ቡና አሰላለፍ

30 ሲሳይ ባንጫ 

5 ጀሚል ያዕቆብ – 12 ቢያድግልኝ ኤልያስ – 21 በኃይሉ በለጠ – 2 ኄኖክ ኢሳይያስ

 23 ኄኖክ ካሳሁን – 4 ሀይደር ሸረፋ  

16 ኪዳኔ አሰፋ – 11 ዳዊት ተፈራ – 9 አሜ መሀመድ 

17 መሀመድ ናስር


ተጠባባቂዎች

1 ጀማል ጣሰው 

14 ሂድር ሙስጠፋ

18 ኃይለየሱስ ብርሀኑ

27 ክሪዚስቶም ንታንቢ

10 ቴዎድሮስ ታደሰ

19 ልደቱ ጌታቸው

24 ቢንያም ትዕዛዙ

11፡45 አሁን የሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች ወደመልበሻ ክፍል ገብተዋል ።


11፡30
ተጨዋቾች እና ዳኞች ወደሜዳ ገብተው ማሟሟቅ ጀምረዋል ።

ዳኛ
የእለቱን ጨዋታ ፌዴራል አርቢትር ማናዬ በዋና ዳኝነት የሚመራው ይሆናል ።

ጤና ይስጥልኝ ክቡራት እና ክቡራን !


የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ደደቢት ከ ጅመማ አባ ቡና በሚያደርጉትን ጨዋታ ዋና ዋና እንቅስቃሴዎች በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር !

7 thoughts on “ደደቢት ከ ጅማ አባ ቡና | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

 • March 26, 2017 at 8:07 pm
  Permalink

  ከተማ ሲያረጅ ጅማን

  ልጅ ሲበላሽ የአባ ጂፋርን ይመስላል አሉ፡፡ አባቴ አሁን የዚህ ዓይነት ስድብ በሶሻል ሚዲያ ይፃፋል፡፡ ቢያንስ ብትበሳጭ እንኳ ቃላት ምረጥ፡፡


  ኳስ ደጋፊ የኳስ እንጂ የብልግና ቃል አይጠቀሙም ፡፡

  ለማንኛውም ከተናደድክብኝ ይቅርታ !!! እንዳትሳደብ ደሞ

 • March 26, 2017 at 7:02 pm
  Permalink

  ababuna ke ireft behuala yigebabetal yeteleye tinkake kalaregu. Gn be counter attack ababuna ketetekemu , betechemari goal mashenef yichlalu

 • March 26, 2017 at 6:24 pm
  Permalink

  ከኢትዮጵያ ዳኞኝ ይልቅ ባዶ ሜዳ ያለዳኛ ብንጫወት ኳሳችን ይለወጥ ነበር
  ደደቦች ስልጠና አይወስድም ዝም ብሎ ጉቦ እየበሉ ከሚዳኙ

Leave a Reply

error: