ከፍተኛ ሊግ | ሀዲያ ሆሳዕና 6 ነጥቦች ቅነሳ ተወሰነበት

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በቅርብ አመታት ከባድ የሚባለውን የቅጣት በትር ሀዲያ ሆሳዕና ላይ አሳርፏል፡፡

በ18ኛው ሳምንት ከስልጤ ወራቤ ገር በተደረገው ጨዋታ 36ኛው ደቂቃ ላይ የሀድያ ሆሳዕና ደጋፊዎች ድንጋይ በመወርወር ለ25 ደቂቃዎች እንዲቋረጥ በማድረግ ፤ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላም ረብሻ በመፍጠር ፣ የፀጥታ ሀይሎች ላይ ጥቃት በማድረስ ፣ ዳኞች ከሜዳ እንዳይወጡ በመከልከል እና መሰል ስፖርታዊ ጨዋነት ግድፈቶች መፈጸማቸው በእለቱ ኮምሽነር ሪፖርት ከመቅረቡ በተጨማሪ የክለቡ ደጋፊዎች ዘንድሮ ብቻ ከሻሸመኔ ከተማ ፣ ወልቂጤ ከተማ እና ጂንካ ከተማ ጋር በፈጸሙት ከስፖርታዊ ጨዋነት ያፈነገጠ ተግባር በተጣለባቸው ቅጣቶች ትምህርት ሳይወስዱ በድጋሚ ወደዚህ ተግባር በመመለሳቸው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በዲሲፕሊን መመርያው ላይ የተቀመጠውን ደንብ በመጥቀስ ክለቡ ካለው ነጥብ ላይ 6 ነጥቦች እንዲቀነሱበት ሲወስን በ30 ቀናት ውስጥ ክለቡ ለደጋፊዎቹ የስፖርታዊ ጨዋነት ግንዛቤ ማስጨበጫ በመስጠት ሪፖርት እንዲያደርግ ተወስኖበታል፡፡

ሀዲያ ሆሳዕና በቅጣቱ መሰረት ከነበረው 33 ነጥብ ወደ 27 ነጥቦች ሲወርድ ደረጃውም ከ3ኛ ወደ 7ኛ አሽቆልቁሏል፡፡

10 thoughts on “ከፍተኛ ሊግ | ሀዲያ ሆሳዕና 6 ነጥቦች ቅነሳ ተወሰነበት

 • April 30, 2017 at 10:18 am
  Permalink

  be ethiopia wonjelegna lay ye moti fird biferedim tegibarawi ayihonem, be egir kuas yenetib kinesa hig eskahun altefetsemem! Hadiya hosana ye Italy club newu inde?

 • April 28, 2017 at 10:05 am
  Permalink

  ማን ነህ ጋሽ ጁነዲን በቡናና በዳሸን እንዲሁም በመሰል ጫወታዎች በተነሳው ብጥብጥ እንኳን ያልተቀነሰው ነጥብ ዛሬ ሃድያ ሆሳዕና ላ ይ መቀነስ የሚጀምረው፤ ለነገሩ አልፈርድም ግልፅ በሆነ የኢ/ያ ኳስ።

 • April 28, 2017 at 9:44 am
  Permalink

  በሀድያ ሆሳዕና የእግር ኳስ ቡድን ላይ የተወሰነው ውሳኔ ክለቡ ውጤታማ ጉዞ እንዳያደርግ ተስቦ የተደረገ ይመስለኛል።የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያስተላለፈውን ውሳኔ መልሶ ቢያጤነው የተሻለ ይሆናል።በመሆኑ የሀድያ ሆሳዕና እግር ኳስ ቡድን ደጋፊ ተብሎ የተላለፈው ውሳኔ ፌዴሬሽኑ ሳያጤን በመሆኑ በደንብ ማየት አለበት እላለሁ።

 • April 27, 2017 at 8:01 pm
  Permalink

  ኧረ ጉድ ነው።የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እውነት በትክክለኛ አመራር ይመራል ወይ?ባለፈው የውድድር ዓመት በኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ በተፈጠረው የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለት የሰው ህይወት አልፏል፣ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።ግን ያኔ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ውሳኔው ምን ነበር?+በጣም የሚገርምና አሳዛኝ ውሳኔ ነው በሀዲያ ሆሳዕና የእግር ኳስ ቡድን ላይ የተላለፈው።

 • April 27, 2017 at 4:31 pm
  Permalink

  ጥያቄ ለእግር …….ፌደሬሽን. በእቅድ የያዛችሁት ከቅጣት የሚገኝ ገቢ ማሳደግ ሲገርመኝ ነጥብ በመቀነስ የሚገኝ ገቢም አላችሁ እንዴ? አረ ጋሽ ጁነዲን አፉ ይበሉን!!!

 • April 27, 2017 at 1:32 pm
  Permalink

  እግርኳስ ፌዴሬሽኑ ሀዲያ ሆሳዕናን ለመጉዳት ሆን ብሎ የወሰነው ውሳኔ ነው፡፡ማንም ክለብ ነጥብ ተቀጥቶ አያውቅም ሪፖርቱ በደንብ ይጣራልን የጨዋታው ኮሚሽነር ከሜዳው ውጭ ለነበረው ክስተት ሪፖርት ማድረግ አይችልም የእሱ ስልጣን 90+ ባሉት የጨዋታ ደቂቃዎች ብቻ ነው፡፡ፌዴሬሽኑ በማይመለከተው እጁን እያስገባ ነው፡፡ውሳኔው ከእግርኳስ ህግ ውጭ ነው፡፡

 • April 27, 2017 at 12:13 pm
  Permalink

  This is really unfair and unjust decision!!! This sounds against not only the Team Hadiay Hosanna but also country’s football. Hope they’ll reflect and come to a right investigations and fair decisions.

Leave a Reply

error: