መቐለ ከተማ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾች አስፈረመ

አዲሱ የፕሪምየር ሊግ ክለብ መቐለ ከተማ ጫላ ድሪባ እና ታደለ ባይሳን የግሉ አድርጓል፡፡

ጫላ ድሪባ አዳማ ከተማን ለቆ የተጠናቀቀውን የውድድር አመት በወልድያ ያሳለፈ ሲሆን ከበድሩ ኑርሁሴን ጋር በመፈራረቅ በወልዲያ አጥቂ መስመር ላይ ከአንዷለም ንጉሴ ጋር ሲሰለፍ ቆይቶ ኮንትራቱን በማጠናቀቁ ወደ መቐለ ተጉዟል ፡፡

ሌላው ለክለቡ የፈረመው ታደለ ባይሳ ነው፡፡ ከፋሲል ከተማ ጋር ወደ ፕሪምየር ሊጉ አብሮ ያደገው የመሀል ተከላካዩ ታደለ ዘንድሮ የሊጉ ክስተት በነበረው ፋሲል ከተማ በስፍራው ከከድር ኸይረዲን ጋር በመፈራረቅ የተጫወተ ሲሆን በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ቡድኑን በአምበልነት ሲመራ እንደነበር ይታወሳል፡፡

መቐለ ከተማ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደጉን ካረጋገጠ ወዲህ በተጫዋቾች ዝውውር ላይ ተሳትፎን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን የሁለቱን ተጫዋቾች ጨምሮ እስካሁን ያስፈረማቸው ተጫዋቾች ቁጥር 5 ደርሷል፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *