ከነአን ማርክነህ ወደ አዳማ ከተማ ተመልሷል

ከነአን ማርክነህ አአ ከተማን ለቆ ወደ ቀድሞ ክለቡ አዳማ ከተማ የሚያደርገውን ዝውውር ዛሬ አጠናቋል፡፡

ከነአን በአዲስ አበባ ከተማ ቀሪ የአንድ አመት ኮንትራት መኖሩን ተከትሎ ክለቡ ለኮንትራት ማፍረሻ የጠየቀውን 200,000 ብር በመክፈል መልቀቂያውን ተቀብሎ ወደ አዳማ ከተማ አምርቷል፡፡ በክለቡም ለ2 አመታት የሚያቆየውን ውል ፈርሟል፡፡

ከነአን የአዳማ ተስፋ ቡድን አባል የነበረ ሲሆን በ2008 ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አምርቶ ባሳየው ብቃት ለኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለመመረጥ ችሎ ነበር፡፡ የተጠናቀቀው የውድድር አመትንም ከሊጉ በወረደው አዲስ አበባ ከተማ አሳልፏል፡፡

አዳማ ከተማ በዝውውር መስኮቱ ከከንአን በተጨማሪ አላዛር ፋሲካ ፣ አንዳርጋቸው ይላቅ እና ዳንኤል ተሾመን ሲያስፈርም ክሪዚስቶም ንታምቢ ለቡና እና አዳማ በመፈረሙ የፌዴሬሽኑ ውሳኔ ይጠበቃል፡፡

ዳንኤል መስፍን

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ዳንኤል መስፍን ነኝ

ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ ምልክት ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ

One thought on “ከነአን ማርክነህ ወደ አዳማ ከተማ ተመልሷል

  • August 4, 2017 at 2:35 pm
    Permalink

    kenean ahun ketesfa yadgal teblo kemitebekew fuad gar tiru timret 2010 lay yasayalu

    Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *