ቻን 2018 | የኢትዮጵያ እና ሱዳን ጨዋታ የሚደረግበት ቀን ታውቋል

ኬንያ በ2018 ለምታስተናግደው የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮና (ቻን) ለማለፍ የሚደረጉ የመጨረሻ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎች ሳምንት ይደረጋሉ፡፡ ካፍ ጨዋታዎች የሚደረጉበት ቀን እና ጨዋታውን የሚመሩ ዳኞችንም ሐሙስ እለት ይፋ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ እና ሱዳን ጨዋታ እሁድ ነሃሴ 7 በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ይደረጋል፡፡ እንደካፍ መረጃ ከሆነ ጨዋታው 10፡00 ሰዓት ላይ ሲደረግ ዩጋንዳዊያን ዳኞች ጨዋታውን ይመራሉ፡፡ ዋና ዳኛ አሌክስ ሙሃቢ ንሱሉምቢ እና ረዳቶቻቸው ማርክ ሶኖኮ፣ ባሊኮዋ ሙሳ ንጎቢ እና መሱድ ሳሉ ጨዋታውን እንዲመሩ በካፍ ተመርጠዋል፡፡ የመልስ ጨዋታው የሚደረግበት ከተማ፣ ቀን እና ሰዓት ካፍ ወደፊት እንደሚገልፅ ከመጠቆሙ ውጪ ያለው የነገር የለም፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቅዳሜ ሉሳካ ላይ ከዛምቢያ ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ ለማድረግ ሐሙስ ወደ ስፍራው ተጉዟል፡፡ ከጨዋታው በኃላ እሁድ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ሱዳንን ለመግጠም የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *