የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ከነገው ጨዋታ በፊት ዛሬ የመጨረሻ ልምምዱን ሰርቷል

ሀሙስ ረፋድ 5:00 ሰአት ላይ ሀዋሳ ገብቶ ማረፊያውን ሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል ያደረገው የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከሰአት 10:00 ሰአት ላይ የመጨረሻ ልምምዱን ሰርቷል፡፡ በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታድየም ባደረገው የአንድ ሰአት ልምምድም በመስመር የማጥቃትና የቆሙ ኳሶች ላይ ያተኮረ ስራን ሰርቷል፡፡

አሰልጣኝ መሀመድ አህመድ አብደላ ‘ማዝዳ’ 24 ተጫዋቾችን በስብስባቸው ውስጥ አካተው ወደ ሀዋሳ የመጡ ሲሆን አራት ተጫዋቾችን ከታላላቆቹ ኤል ሜሪክ እና አል ሂላል እንዲሁም በካፍ ኮንፌድሬሽንስ ዋንጫ ቲፒ ማዜምቤን በቀጣይ ቀናት ከሚገጥመው አል ሂላል ኦቤይድ 6 ተጫዋቾችን መርጠዋል፡፡ በአጠቃላይ አሰልጣኝ መሐመድ አብደላ ከዋናው ብሔራዊ ቡድን ይልቅ በርካታ ተጫዋቾች ከ23 አመት በታች ቡድን የመረጧቸው ናቸው፡፡

የሱዳን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ መሐመድ አህመድ አብደላ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ከደቂቃዎች በኃላ ወደናንተ የምናደርስ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *