ከፍተኛ ሊግ | ሀምበሪቾ አስራ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾች አስፈርሟል

በ2010 ወደ ከፍተኛ ሊግ ያደገው ሀምበሪቾ ዱራሜ ባለፈው ዓመት ጥሩ የውድድር ጊዜ በማሳለፍ 7ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን ለዘንድሮው የውድድር ዓመት ቡድኑን ለማጠናከር የፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን አስፈርሟል። 

በምድብ (ደቡብ ምዕራብ) የለተደለደለው ሀምበሪቾ በ2010 ግማሽ ሻሸመኔን ለቆ ቡድኑን ከተረከበው ያሬድ አበጀ ጋር የሚቀጥል ሲሆን ራሱን በተሻለ ሁኔታ ለውድድሩ ብቁ አድርጎ ለመቅረብ የውድድር ሜዳውን ለተመልካች ምቹ ከማድረግ እንዲሁም በስታዲዮሙ ዙሪያ ያሉ መስረተ ልማቶች መሰራታቸውን ክለቡ ገልጿል። በቀጣይም ከደጋፊዋቻቸው ጋር በመሆን በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ አተኩረው እንዲሚሰሩ የክለቡ የቡድን መሪ አያይዘው ገልፀዋል:። 

ሀምበሪቾ የነባር 8 ተጫዋቾችን ውል ሲያድስ ሁለት ተጫዋቾችን ከወጣት ቡድን ማሳደግ ችሏል። በፊርማ ወደ ቡድኑ የተቀላቀሉት ተጫዋቾች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡-

መቆያ አልታየ (ነጌሌ ከተማ /ተከላካይ)፣ ያያ ዓለሙ (ደቡብ ፖሊስ/ተከላካይ)፣ በረከት ቦጋለ (አርባምንጭ/ተከላካይ)፣ አብነት ተሾመ (ሀላባ/አማካይ)፣ ተስፋሁን ተሰማ እና ፋሲል (ከሻሸመኔ/አማካይ)፣ ወንድሜነህ ዘሪሁን (ደቡብ ፖሊስን ተቀላቅሎ የነበረ ቢሆንም ተለያይቷል። )፣ ፀጋ (ደቡብ ፖሊስ/ አማካይ)፣ ምንተሰኖት ዳልጋ (አዋሳ ተስፋ/ አጥቂ)፣ ሚካኤል ወልደሩፋኤል (ወልቂጤ/ አጥቂ)፣ መልካሙ ፉንድሬ (ስልጤ ወራቤ/አጥቂ)፣ ዘካርያስ ፍቅሬ (አርባምንጭ/አጥቂ)

error: