የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ትላንት ምሽት የመጨረሻ ልምምዱን አደረገ

የማሊ አቻውን ሊገጥም ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን ወደ ማሊ ዋና ከተማ ባማኮ የተጓዘው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ሰኞ ምሽት የመጨረሻ ልምምዱን በስታድ ሞዲባ ኬይታ አድርጓል።

ልምምዱን ለማድረግ ቀደም ብሎ በስታዲየሙ የተገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሜዳው ላይ ይካሄድ በነበረው የአትሌቲክስ ውድድር ምክንያት አምሽቶ ለመስራት ተገዷል። ከዛም በተጨማሪ ተመልካች፣ ጋዜጠኛና የተቃራኒ ቡድን አሰልጣኞች ቡድን አባላት እንዲወጡለት ቢጠይቅም በእምቢተኝነት ምክንያት ልምምዱን በተመልካች ፊት ለማድረግ ተገዷል። የጨዋታው ሰዓትም ቢሆን ቀድሞ ይደረግበታል ከተባለበት ምሽት 1 ሰዓት ወደ 11 ሰዓት የተቀየረ ሲሆን ይህም ባለሜዳዎቹ የባማኮን ከፍተኛ ሙቀት ለመጠቀም ያሰቡ ይመስላል።

አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ “ምንም እንኳን ይህ ድርጊት ቢፈፀምብንም ውጤት ይዞ ለመውጣት ጥረት እናደርጋለን። ቡርኪናፋሷዊው ኮሚሽነር በልምምዱ ወቅት የተፈጠረውን ሁኔታ ለማስተካከል ጥረት በማድረጉ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ። ” ሲሉ በአዲስ አበባ ስታዲየም ማሊ ላይ የአቻነቷን ግብ ያስቆጠረው ደስታ ደሙ እንዲሁም አጥቂው ፍቃዱ ዓለሙ በተመሳሳይ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት የአየር ፀባዩ እጅጉን ሙቀታማ በመሆኑ እንደከበዳቸው ነገር ግን በድል ለመወጣት ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ወደ ማሊ የተጓው ስብስብ ከጉዳት ነፃ እንደሆነ ሲገለፅ ጊኒያዊ ዜግነት ያላቸው ዳኞች የሚመሩት ይሆናል።

በመጀመርያው ጨዋታ 1-1 ደዲስ አበባ ላይ የተጠናቀቀው ጨዋታን በደርሶ መልስ የበላይ ሆኖ የሚያጠናቅቀው ቡድን በቀጣይ ዙር ከካሜሩን ይጫወታል።

በተሾመ ፋንታሁን እና ቴዎድሮስ ታከለ


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *