የአሰልጣኞች አስተያየት | መቐለ 70 እንደርታ 1-1 ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ትኩረት አግኝቶ የነበረው የመቐለ እና ወልዋሎ ጨዋታ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች የሚከተለውን ብለዋል።
“በቀጣይም ልንሸነፍ እንችላለን፤ ቻምፒዮን የሚደርገን ግን አጠቃላይ ውጤታችን ነው” ገብረ መድኅን ኃይሌ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው የደርቢ መልክ ነበረው። ሁሉም የራሱ የጨዋት እቅድ ይዞ ነው የሚመጣው። እኛ አጥቅተን ለመጫወት ነው የገባነው። በተደጋጋሚ ያገኘነውን ድል አስጠብቆ ለመሄድ እና መሪነታችን ለማጠናከር ነበር እቅዳችን። ወልዋሎዎች መጀመርያ ነው ያገቡብን፤ ከኃላ ትነስተን ጎሎች አስቆጥረን ማሸነፍ ከብዶናል። የተወሰኑ ክፍተቶች ነበሩብን። በአጠቃላይ ሲታይ ግን አስከፊ አይደለም። ጨዋታው በሰላም ማለቁ ትልቅ ድል ነው።

ስለ ቀጣይ ጨዋታዎች

እግር ኳስ አንዴ ታሸንፋህ አንዳዴም ልትሸነፍ ትችላልለህ። አስር ተከታታይ ድሎች አስመዝግበን መጥተናል። ይሄ ከባድ ነገር ነው። ዛሬ አቻ የወጣነው ሊያጋጥመን ከሚችሉት ነገሮች አንዱ ነው። የደርቢው ስሜት ይዞት የመጣ ነገር ነው። በቀጣይም ልንሸነፍ እንችላለን። ግን ቻምፒዮን የሚደርገን አጠቃላይ ውጤታችን ነው።
እንጂ አንዴ ስላሸነፍክ ዝም ብለህ እስከመጨረሻው ታሸንፋለህ ማለት አይደለም።
በቀጣይም ያለውን ነገር አስጠብቆ ለመሄድ አሁን ቀጣይ ከባድ ጨዋታ ነው ያለብን። እሱን ጨዋታ በተቻለን መጠን ጥሩ ውጤት ይዘን ለመምጣት እንጥራለን።

“በጊዜ ስላገባን ያን የማመን ችግር ነበረብን”
ዮሃንስ ሳህሌ

የቀድሞ ቡድናቸው መግጠማቸው የፈጠረባቸው ስሜት

ስሜቱ ቅልቅል ነው። ባለፈው ዓመት ስታሰለጥነው የነበረውን ቡድን እና ስታሰለጥናቸው የነበሩ ተጫዋቾችን በተቃራኒ መግጠም ከባድ ነው። ግን ይህ እግር ኳስ ነው። ከምንም በላይ ግን የትግራይ እግር ኳስ የት እንደደረሰ እየታየ ነው። እንዲህ አይነት ደጋፊ በየትኛውም ቦታ አይታይም።
ከበድ ያለ ጨዋታ ነበር። ምክንያቱም የነበረን የዝግጅት ግዜ አጭር ነበር። ቢሆንም ግን የራስ መተማመን ችግር ነበረብን እንጂ ዛሬ ከዚ በላይ መስራት እንችል ነበር። መቐለ በአሁን ሰዓት ያለበት ደረጃ እና በዚ አስፈሪ ደጋፊ ፊት ስትጫወት ከበድ ይላል።

በውጤቱ ስለተሰማው ነገር

በውጤቱ ደስተኛ አይደለሁም። በልምምድ ከሰራነው አንፃር የተሻለ ነገር ማድረግ እንችል ነበር። አሁንም ግን የዚህ ደጋፊ ተፅዕኖ ከባድ ነው።
ያንን መቋቋም አስቸግሮናል። ከዛ ውጭ ግን የኛ ተጫዋቾች ከዚ የተሻለ ማድረግ ይችሉ ነበር። ከዚ የተሻለ አቅም አላቸው። ግን የመጣው ውጤትም አስከፊ አይደለም።

የሊጉን መሪ የመግጠም ተፅእኖ

አዎ ቅድምም ብዬዋለው ከባድ ጫና አለ።
በጊዜ ስላገባን ያንን የማመን ችግር ነበር።
ገና 19 ደቂቃ ላይ ጎል አግብተህ ያንን አስጠብቀህ መውጣት ማሰብ ልክ አይደለም። መጫወት ነበረብን ፤ ግን ቅድም እንዳልኩህ የዚ ደጋፊ ተፅዕኖ ቀላል አይደለም በጣም በጣም ከባድ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *