ወልዋሎዎች አዲሱ ድረ ገፃቸውን ዛሬ አስመረቁ

ቢጫ ለባሾቹ በኤዲዮ ኮሙኒኬሽን አማካኝነት ያሰሩት የኦን ላይን ግብይት ያጠቃለለው ድረ ገፅ ዛሬ በፕላኔት ሆቴል አስመረቁ።

ይጀመራል ከተባለበት ሰዓት ዘግይቶ በተጀመረው የምረቃ እና ይፋዊ ስራ ማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓት የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቶ ዛይድ ነጋሽ (ዶክተር) ጨምሮ በርካታ እንግዶች በተገኙበት ነበር የተካሄደው። የወልዋሎው ፕሬዝዳንት አቶ መርሃዊ ኃይለደሥላሴ ባደረጉት ንግግር የጀመረው ስነ-ስርዓቱ ብዙ ዝርዝር ሃሳቦች የተነሱበት ነበር። በተለይም አቶ መርሃዊ አሰራሩ ቡድኑ ላይ ተአማኒነት እና ግልፅ አሰራር የሚያሰፍን በመሆኑ ተመራጭ እንደሚያደርገው ገልፀው ቴክኖሎጂው ለቡድኑ በነፃ ያስረከበው ኤድዮ ኮሙኒኬሽንን አመስግነዋል።

ከመክፈቻው ንግግር በኃላ ስለ ቴክኖሎጂው አጠቃላይ መግለጫ የሰጡት የኤዲዮ ቴክኖሎጂ አባላት ሲሆኑ አሰራሩ ግልፅ እና ተአማኒ ከመሆኑ አልፎ ለአጠቃቀም ቀላል መሆኑ አስረድተዋል።
ከምረቃው በኃላም በርካታ የክለቡ ደጋፊዎች ሄሎ ካሽ በመጠቀም የኦንላይን ግብይት አድርገዋል። ከዚ በተጨማሪ ቡድኑ በድረ ገፁ (www.welwalofc.com) አማካኝነት የገንዘብ ድጋፎች እየተደረጉለት ይገኛል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: