የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች ወደ ልምምድ ተመልሰዋል

በደመወዝ ጥያቄ ምክንያት ለአንድ ሳምንት ከልምምድ ርቀው የነበሩት የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋቾች ወደ ልምምድ ተመልሰዋል።

ጅማ አባጅፋሮች ባለፈው ሳምንት እሁድ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ከተጫወቱ በኋላ ወደ ልምምድ መርሐ ግብር አለመመለሳቸው የሚታወስ ሲሆን በኢትዮጵያ ዋንጫ አንደኛ ዙር እና የፕሪምየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ከወላይታ ድቻ ጋር የነበረባቸውን ጨዋታም ወደ ስፍራው ባለማቅናታቸው ፍርፌ እንደሰጠባቸው የሚታወስ ነው።

የቡድኑ አመራሮችና ተጫዋቾች ያሳለፍነው ቅዳሜ ባደረጉት ስብሰባ ቅድሚያ የአንድ ወር ደመወዝ፤ በሚቀጥሉት ቀናት ደግሞ ቀሪ ያለከፈለ ደመወዛቸው እንደሚከፈላቸው ቃል በተገባላቸው መሰረት በቀጣይ በ28ኛ ሳምንት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ዝግጅታቸውን ዛሬ 09:00 ላይ ባከናወኑት የልምምድ መርሐ ግብር ጀምረዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: