የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከናሚቢያ እግር ኳስ ማኅበር ጋር አብሮ ለመስራት ተስማማ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ናሚቢያን ለመደገፍ ወደ ግብፅ የሚያመሩ ደጋፊዎችን ለማጓጓዝ ከሀገሪቱ የእግር ኳስ ማኅበር ጋር ውል አሰረ።

ከ2008 የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በሪካርዶ እየተመሩ ከምድባቸው ጊኒ ቢሳውን ተከትለው ወደ አፍሪካ ዋንጫ ያለፉት ‘ብሬቭ ዋርየርስ’ ከበርካታ ዓመታት በኃላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለማምራት በዝግጅት ላይ የሚገኙት ደጋፊዎቻቸውን ወደ ግብፅ ለማጓጓዝ ከኢትዮጽያ አየር መንገድ ጋር ይፋዊ ስምምነት ፈፅመዋል።

በትላንትናው ዕለት ከእግርኳስ ማኅበሩ ጋር ስምምነት የፈፀመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአህጉሪቱ ባለው ጥሩ ስም እና ከአዘጋጅዋ ሃገር ባለው የርቀት ቅርበት ምክንያት የበርካታ ሃገራት ቀዳሚ ምርጫ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

እንደሚታወቀው አየር መንገዱ ባለፈው ሳምንትም የሊቨርፑል ደጋፊዎች ለአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ወደ ማድሪድ በጥሩ ሁኔታ ማጓጓዙን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስሮች ከክለቡ ደጋፊዎች ብዙ ምስጋና ደርሶታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡