ደደቢት ተጫዋቾችን ማሰናበቱን ቀጥሏል

ባለፈው ሳምንት ከበርካታ ተጫዋቾች በስምምነት የተለያዩት ሰማያዊዎቹ ከጋናዊው ግብጠባቂ ዓብዱልረሺድ ማታውኪል ጋርም ተለያይተዋል።

በዓመቱ መጀመርያ በደደቢት ለአንድ ዓመት ለመቆየት በመስማማት ቡድኑን የተቀላቀለው ዓብዱልረሺድ ማታውኪል የውድድር ዘመኑን ሳይጨርስ ተለያይቷል። በመጀመርያው ዙር የቡድኑ ቀዳሚ ተመራጭ የነበረው ግብ ጠባቂው በትግራይ ክልል ዋንጫ ጥሩ ብቃት አሳይቶ የውድድሩ ኮከብ ግብ ጠባቂ የተባለ ሲሆን ፕሪምየርሊጉ ከተጀመረ በኃላ ግን አቋሙ ወርዶ ለብዙ ግቦች መቆጠር ምክንያት መሆኑ ይታወሳል። በሁለተኛው ዙርም በሙሴ ዮሃንስ የቋሚነት ቦታውን ተነጥቆ ቆይቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: