የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ24 ክለቦች መካከል እንዲካሄድ ተወሰነ

(መረጃው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ነው)

የኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ ተብሎ ከተሰየመበት ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ በአንድ ምድብ ተዟዙሮ በሜዳ እና ከሜዳ ውጪ በሚደረግ የደርሶ መልስ ውድድሮችሲካሄዱ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ ይህም በመሆኑ በሀገሪቱኘሪሚየር ሊጉ ይካሄዱባቸው በነበሩ ከተሞች እና አካባቢዎችከፍተኛ መነቃቃትን ፈጥሮ ቆይቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለያዩ የውድድርሜዳዎች ላይ ከፍተኛ የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል እየታዩመምጣታቸው የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡፡ ይህም ሊሆን የቻለውበየአካባቢው የሚንፀባረቁ የፓለቲካ አጀንዳዎች ወደ ውድድር ሜዳበመምጣታቸው መሆኑ የማይደበቅ ሀቅ ነው፡፡ በመሆኑም ይህንንችግር መቀነስ ላይ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጶጉሜ 1 ቀን 2011 ዓ.ምባደረገው ስብሰባ በ2012 ዓ.ም የኘሪሚየር ሊግ አካሄድ ላይ ሰፊውይይት ካደረገ በኋላ ውድድሮች መካሄድ ያለበትን አቅጣጫአስቀምጧል፡፡

በዚሁ መሠት በ2012ዓ.ም የኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ ተሳታፊክለቦች፡-

1. በ2011ዓ.ም የኘሪሚየር ሊግ ተሳታፊ የነበሩ 16ቱም ክለቦች

2. በ2011ዓ.ም ከሱፐር ሊግ ውድድር ወደ ኘሪሚየር ሊግ ያለፉ3 ክለቦች

3. በ2011ዓ.ም ከሱፐር ሊግ ውድድር ከየምድባቸው 2ኛ የወጡ 3 ክለቦች

4. በ2011ዓ.ም በሱፐር ሊግ ከ3ቱም ምድብ 3ኛ ከወጡት የተሻለ ነጥብ ያላቸው 2 ክለቦች ሲሆኑ ቁጥራቸውን ሀያ አራት (24) በማድረግ በሁለት ምድብ ተከፍለው እንዲጫወቱ ተወስኗል፡፡ የምድብ አደላደሉም በሊግ ኮሚቴ አማካኝነት ለክለቦቹ የሚቀርብ ይሆናል፡:


© ሶከር ኢትዮጵያ