ፌደሬሽኑ ይቅርታ ጠየቀ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋልያዎቹ ለደረሰባቸው እንግልት ይቅርታ በመጠየቅ ብሄራዊ ቡድኑ ወደ ምድብ ድልድል በመግባቱም ሽልማት አበርክቷል።

ዋልያዎቹ ሌሶቶን ከሜዳ ውጭ ጎል ህግ አሸንፈው ወደ ምድብ ማጣርያ መግባታቸውን ካረጋገጡ በኃላ በተፈጠሩ የአሰራር ክፍተቶች ብሔራዊ ቡድኑ ባልተመቻቸ ሁኔታ እዛው ለመቆየት እንደተገደደ ይታወቃል። ትላንትም እግር ኳስ ፌደሬሽኑ ለተፈጠሩት ነገሮች ይቅርታ ጠይቆ ጥፋተኛ ባላቸው ግለሰቦች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።

እንደ ፌደሬሽኑ ይፋዊ ድረ ገፅ ዘገባ አቀባበሉ ላይ በርካታ የፌደሬሽኑ የበላይ አካላት የተገኙ ሲሆን የቡድኑ አምበል ሽመልስ በቀለ እና ዋና አሰልጣኙ አብርሃም መብራቱም ጉዞው አስመልክተው በመድረኩ ሃሳባቸው ገልፀዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ