የሳላዲን ሰዒድ ጉዳት ደጋፊውን አስግቷል

ለረጅም ወራት ከሜዳ ከራቀ በኃላ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ ድንቅ አቋም ያሳየው አንጋፋው አጥቂ ሳልሀዲን ሰዒድ በጉዳት ምክንያት ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል።

ጉዳት የእግርኳስ ህይወቱን እየተፈታተነው የሚገኘው ሰልሀዲን ሰዒድ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰበታ ከተማን ባስተናገደበት ጨዋታ በ76ኛው ደቂቃ የጡንቻ መሳሳብ ጉዳት አጋጥሞት በጋዲሳ መብራቴ ተቀይሮ መውጣቱ ይታወቃል።

ሳልሀዲን ከጉዳቱ አገግሞ ዳግም ወደ ሜዳ ለመመለስ ከሁለት እስከ ሦስት ሳምንት በቂ እረፍት የሚያስፈልገው በመሆኑ ፈረሰኞቹ በቀጣይ ከወላይታ ድቻ፣ ሱሑል ሽረ እና ከጅማ አባ ጅፋር ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ላይደርስ እንደሚችል ተገልጿል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: