ሎዛ አበራ በአንድ ጨዋታ ሰባት ግቦች አስቆጠረች

ቢርኪርካራዎች ሄበርንያንስን አስራ ሰባት ለባዶ በረመረሙበት ጨዋታ ሎዛ አበራ ሰባት ግቦች አስቆጠረች።

በማልታ አስደናቂ ብቃት በማሳየት የታላላቅ መገናኛ ብዙሃን ቀልብ የሳበችው ሎዛ አበራ በማልታ ቆይታዋ ከሳምንታት በፊት ሃትሪክ ስትሰራ ዛሬም ሱፐር ሃትሪክ ሰርታለች። በሁለተኛው ዙር የማልታ ፕሪምየር ሊግ በሜዳቸው ሂበርንያንስ የገጠሙት ቢርኪርካራዎች ተጋጣምያቸውን አስራ ሰባት ለባዶ አሸንፈዋል። ሎዛ አበራ በአስራ አምስተኛው ፣ በሰላሳኛው ፣ በአርባ አምስተኛው እና ሃምሳ ስድስተኛው ደቂቃዎች አራት ግቦች ስታስቆጥር የተቀሩት ሶስት ግቦች ደሞ በሶስት ደቂቃ ባልሞላ ግዜ ውስጥ አስቆጥራለች። የተቀሩት ግቦች ደግሞ በስቴፈን ፋሩግያ (2) ፣ ቬሮኒክ ሚፍሱድ(2) ፣ ቴሬሲ ቱማ ፣ አይሻ ሱልጣን(2) ሲሞኒ ቡቲጌግ ፣ ራይና ጉስቲ እና ጋብርኤላ ዛሃራ የተቆጠሩ ናቸው።

ከሳምንታት በፊት ከሞስታ ጋር በነበረው ጨዋታ ሐት-ትሪክ የሰራችው ሎዛ የዛሬ ሰባት ግቦችን ጨምሮ በማልታ ቆይታዋ በሰባት ጨዋታዎች አስራ ሰባት ግቦች ስታስቆጥር የሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትም እየመራች ትገኛለች።


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: