የአሰልጣኞች አስተያየት | ቅዱስ ጊዮርጊስ 3-2 ድሬዳዋ ከተማ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከተማን 3-2 ካሸነፈበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኃላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።

👉 “በትኩረት ማነስ ብዙ እድሎች ሰጥተናቸው ነበ” ሰርዳን ዝቪጅኖቭ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

“ዛሬ ስታዲየም ጨዋታውን ለመከታተል የመጡ ተመልካቾች በተቆጠሩት ግቦች ብዛት ደስተኛ ናቸው ብዬ አስባለሁ፤ በመጨረሻዎቹ 10 ደቂቃዎች ትኩረታችንን አጥተን ነበር በዚህም የተነሳ ሁለት ግቦች አስተናግደናል። እስከ 7ኛው ሳምንት በነበረን ጉዞ በጨዋታዎች ላይ ብዙም ግቦች አናስተናግድም ነበር። ዛሬ ግን ሁለት ተቆጥሮብናል ይህ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው።

በመጀመሪያ አጋማሽ ጥሩ ነበርን በጥሩ የጨዋታ ቅፅበት ግብ ማሶቆጠራችን ጠቅሞናል ፤ በሁለተኛው አጋማሽ የመጀመሪያ 30 ደቂቃዎች ጨዋታውን ተቆጣጥረን ነበር ከዛ ግን በትኩረት ማነስ ብዙ እድሎች ሰጥተናቸው ነበር።”



👉 “ውጤቱ የሚገባን አልነበረም” ስምዖን ዓባይ (ድሬዳዋ ከተማ)

ስለጨዋታው

“ጨዋታውን ከእንቅስቃሴ አንፃር የምንለካው ከሆነ ውጤቱ የሚገባን አልነበረም። የነበሩብን ስህተቶችን ዛሬም ማረም አልቻልንም። እንደቀደሙት ጨዋታዎች ሁሉ በጨዋታው የመጀመሪያ ደቂቃዎች ዛሬም ግብ አስተናግደናል። ይህን ለማረም ብዙ ስራዎች ሰርተን ነበር። ነገርግን ዛሬም በተመሳሳይ እነዚሁ ችግሮች ዋጋ አስከፍሎናል። ከምንም በላይ በዛሬው ጨዋታ በቡድኔ ደስተኛ ነኝ። ከምንም በላይ ኳሱን ተቆጣጥረን መጫወት ችለናል፤ ለ90 ደቂቃ በኳስ ቁጥጥር ውስጥ ሆነን ብልጫ መውሰድ ብንችልም ውጤቱ ግን ጨዋታውን ፍፁም አይገልፀውም።

በተደጋጋሚ ጨዋታዎች በመጀመሪያ ደቂቃዎች ግብ ስለማስተናገዳቸው

“ከሁኔታው መደጋጋም የተነሳ ስራዎች እየሰራን ላይመስል ይችላል። ነገርግን በተቻለን አቅም ስራዎችን ለመስራት እየሞከርን እንገኛለን። ይህን ለማረም እየሄድንበት ባለነው አካሄድ ልጆቹን ከፍተኛ ጫና ውስጥ እየከተትናቸው እንገኛለን ይህም ለስህተቶቹ በተደጋጋሚ መከሰት ምክንያት እየሆነብን ይገኛል።”


© ሶከር ኢትዮጵያ