ሁለት የከፍተኛ ሊግ ክለቦች ድጋፍ አድርገዋል

በከፍተኛ ሊግ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት አቃቂ ቃሊቲ እና የካ ክፍለ ከተሞች በቴሌግራም ከቡድን አባላቶቻቸው ጋር ግንኙነት ሲጀምሩ ለኮሮና ቫይረስ የሚውል ድጋፍ አድርገዋል።

የምድብ ሀ ተሳታፊ የሆነው አቃቂ ቃሊቲ በቴሌግራም ግሩፕ በመክፈት ተጫዋቾችን እና የአሰልጣኞችን ስታፍ ያማከለ ስራ እየተሰራ መሆኑን የቡድኑ ዋና አስልጣኝ አቶ ፀጋዬ ወንድሙ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል። በተያያዘም በሀገራችን እየተንሰራፋ የመጣሁን የኮሮና ቫይረስ ተፅእኖን ለመቀነስ የወንድ እና የሴት ቡድን ተጫዋቾች፣ የአሰልጣኞች ቡድን፤ የቡድን መሪዎች፣ ወጌሻዎች እና የቦርድና የቴክኒክ ኮሚቴዎች እና የቡድኑ አካላት መዋጮ በማድረግ ስልሳ ስድስት ሺ ብር (66,000) እንዲሁም የተለያዩ ምግቦችና የፅዳት መጠበቂያ ቁሶች ድጋፍ በማድረግ ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አሥራት መስጠታቸው ተገልጿል።

በምድብ ለ እየተሳተፈ የሚገኘው የካ ክፍለ ከተማ በስፖርቱ ዘርፍ ያሉ ቡድኖች የእግርኳስ፣ የቅርጫት ኳስና የጠረጴዛ ቴኒስ ስፖርት ክለቦች ከአባሎቻቸውና ከአሰልጣኞች 18,550 ብር በማዋጣት ምግቦች እና የምግብ ግብአቶች እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ እንዲሁም ለግሰዋል ለየካ ክፍለ ከተማ አስረክበዋል። በተጨማሪም በቴሌግራም ግሩፕ በመክፈት ተጫዋቾች እና የአሰልጣኞችን ስታፍ ያመከለ ስራ እየተሰራ መሆኑን የቡድኑ ዋና አስልጣኝ አቶ ባንተይርጋ ጌታቸው ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: