የሀዲያ ሆሳዕና ተጫዋቾች ቅሬታ…

ባለፈው ዓመት ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ቆይታ የነበራቸው ተጫዋቾች ከደሞዝ ጋር በተያያዘ ቅሬታቸውን አሰሙ።

ተጫዋቾቹ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት መጀመርያ አከባቢ ከቡድኑ በጎ ምላሾች እያገኙ ደሞዛቸውን በመጠባበቅ ቢቆዩም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን የክለቡ አመራሮች በደሞዙ ዙርያ ለመነጋገር ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። እስከ አራት ወር የሚጠጋ ያልተከፈለ ውዝፍ ደሞዝ እንዳለ የገለፁት የቡድኑ ተጫዋቾች በዚህ ሰዓት በችግር ውስጥ መሆናቸው ሲገልፁ በዚ ወቅት ካጋጠመው ወረርሺኝ ተደማምሮም ሁኔታዎች ከባድ እንደሆኑባቸው ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የክለቡን አመራሮች ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፤ በቀጣይ ቀናትም የክለቡን ምላሽ ይዘን ለመቅረብ ጥረት እናደርጋለን።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ