በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የሚመራው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የቅድም ውድድር ዝግጅት መጀመሩ ታውቋል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ምንም አንኳን ሊጉ ከፋይናንስ ስርዓቱ መመርያ ጥሰት ጋር በተያያዘ የ2017 የውድድር ዘመን የደረጃ ማሻሻያ ተደርጎበት ዘጠነኛ ደረጃ ይዞ እንዲያጠናቅቅ ቢደረግም ቡድኑ ላለመውረድ በሚደረግ ትንቅንቅ ውስጥ በመጨረሻው ጨዋታ ባስመዘገበው ወሳኝ ድል መቆየቱ ይታወሳል።
ለ2018 የውድድር ዘመን የስምንት ተጫዋቾችን ውል አራዝሞ ከአምስት ተጫዋች ማስፈረም ብቻ የቻለው ክለቡ በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ዜጋ ተጫዋቾችን ወደ ማስፈረም ይገባል ተብሎ ይጠበቃል። አሁን ሶከር ኢትዮጵያ እንዳገኘቸው መረጃ ከሆነ ቡድኑ ወደ አዳማ ተጎዞ ዝግጅት የጀመረ ሲሆን በቀጣይ አዲሱ ዓመት መጀመርያ ላይ በሚዘጋጀው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል።