አዳማ ከተማ ጋናዊውን አጥቂ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል

አዳማ ከተማ ጋናዊውን አጥቂ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል

ላለፉት ሁለት ዓመታት በሲዳማ ቡና ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ አዳማ ከተማ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።


በዝውውሩ እጅግ የጎላ እንቅስቃሴ በማድረግ በርከት ያሉ ዝውውሮች በማድረግ ላይ የሚገኙት አዳማ ከተማዎች አሁን ደግሞ ባለፉት ሁለት ዓመታት በሲዳማ ቡና ቆይታ የነበረው ጋናዊው ማይክል ኪፕሩቪ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

በ2017 የውድድር ዓመት በ28 ጨዋታዎች ተሳትፎ
1419′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው አጥቂው በመጀመርያው ዓመት የሲዳማ ቡና ቆይታው ሰባት ግቦች በማስቆጠር ቡድኑ በሊጉ እንዲተርፍ ጉልህ ድርሻ ከተወጡ ተጫዋቾች አንዱ መኖሩ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ከሲዳማ ቡናዎች የነበረው የአንድ ዓመት ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ማረፍያው አዳማ ከተማ ለማድረግ ከስምምነት ደርሷል።

አጥቂው ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ በፊት በሱዳኑ ኤልሜሪክ፣ በአይቮሪኮስቱ አፍሪካን ስፖርትስ፤ በማሊው ክለብ ጃራፍ፤ በቡርኪናፋሶው የኔንጋ ኦጋድጉ እንዲሁም በህንድ ክለቦች ቢ ኤስ ኤስ ስፖርቲንግ እና በኔሮካ መጫወት ችሏል።