አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ ቅጣት ተጣለባቸው

አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ ቅጣት ተጣለባቸው

የውድድር እና ስነስርዓት ኮሚቴ በሽረ ምድረገነት ዋና አሰልጣኝ ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።

በሁለተኛው ሳምንት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣በአራተኛ እና አምስተኛ ሳምንት ደግሞ ከፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና ጋር በተካሄዱ ጨዋታዎች ላይ የማስጠንቀቂያ ካርድ የተመለከቱት የሽረ ምድረ ገነቱ ዋና አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ ከሲዳማ ቡና ጋር ባደረጉት ጨዋታ ያልተመዘገበ የቡድን አባል በምክር መስጫ ቦታ ተገኝቶ በፈፀመው ጥፋት እንዲሁም ከላይ በተጠቀሱት ጥፋቶች ምክንያት ለሦስት ጨዋታዎች እንዲታገዱና 10.000 ብር እንዲከፍሉ የውድድር እና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።