የሴካፋ ዞን ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ የፍጻሜ ጨዋታውን ኢትዮጵያዊው ዳኛ ይመራዋል።
በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በከፍተኛ ድምቀት ያለፉት ቀናት በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የሴካፋ ዞን ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ውድድር ነገ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በሚደረጉ የፍጻሜ እና የደረጃ ጨዋታዎች መዝጊያውን ያገኛል።

ኢትዮጵያ ከኬንያ ከሚያደርጉት የደረጃ ጨዋታ በመቀጠል የሚካሄደውን ተጠባቂውን የታንዘኒያ እና የዩጋንዳን የፍጻሜ ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ እንደሚመራው መረጡን አውቀናል። አብረውት በረዳትነት የጅቡቲ እና የሩዋንዳ ዳኞች የተመረጡ ሲሆን በአራተኛ ዳኝነት ከሱማሌ መመደባቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


