ስብስባቸውን ማጠናከር የቀጠሉት መቻሎች የወሳኝ ተጫዋቻቸውን ውል ሲያራዝሙ ጠዋት ያጋራናቹህ ሦስት ዝውውሮች አመሻሹ ላይ በይፋ ተጠናቀዋል

ለከርሞ ተጠናክረው ለመቅረብ ያሬድ ካሳዬ ፣ ረመዳን የሱፍ እና አማኑኤል ተርፋ ለማስፈረም ተስማምተው የአለምብርሃን ይግዛው ፣ አማኑኤል ዮሐንስ እና ዓብዱልከሪም ወርቁ ውል ያራዘሙት መቻሎች አሁን ደግሞ የሦስት ተጫዋቾችን ውል ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል።
ከአዳማ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ የሊጉን ዋንጫ ባሳካበት ፋሲል ከነማ እንዲሁም ያለፉትን ሁለት ዓመታት በመቻል ቤት ቆይታ ያደረገው በረከት ደስታ ፤ ከዚህ ቀደም በሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን እና አዲስ አበባ ከተማ የተጫወተው የቡድኑ አምበል ዳዊት ማሞ እንዲሁም የመቻል ታዳጊ ቡድን ውጤት የሆነው የፊት መስመር ተጫዋቹ ዮሐንስ መንግሱ በቡድኑ ለመቆየት ከስምምነት የደረሱ ተጫዋቾች ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪ ጠዋት ባደረስናቹህ መረጃ መሰረት ተከላካዩ አለምብርሃን ይግዛው እና አማካዩ አማኑኤል ዮሐንስ በክለቡ ለመቆየት ፌርማቸው ሲያኖሩ የግራ መስመር ተከላካዩ ረመዳን የሱፍ እንዲሁም በኢራቅ ቆይታ የነበረው የመሀል ተከላካዩ አማኑኤል ተርፉ ደግሞ በይፈ ጦሩን ተቀላቅለዋል።


