ወልዋሎ ዛሬ ምሽት 2 ሰዓት የሚያደርገው የካፍ ኮንፌደሬሽን ጨዋታ የቀጥታ ሽፋን ያገኛል

ወልዋሎ እና ሂላል አል ሳሕል የሚያደርጉት የካፍ ኮንፌደሬሽን ካፕ ጨዋታ በሂላል አልሳሕል የፌስቡክ ገፅ በቀጥታ እንደሚተላለፍ ክለቡ በይፋዊ ገፁ አስታውቋል። ወልዋሎ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚያደርገው የአህጉራዊ ጨዋታ ከቀናት በፊት ወደ ሩዋንዳ ኪጋሊ ያመራ ሲሆን ላለፉት ሁለት ቀናት በስፍራው ልምምድ ከሰራ በኋላ ለጨዋታ ዝግጁ እንደሆነ እና ሁሉም የክለቡ ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት እንደሚገኙ የታወቀ ሲሆን በርከት ያሉ የክለቡ ደጋፊዎችም ጨዋታውን ለመከታተል ወደ ከተማው ገብተዋል።

