አፈወርቅ ሀይሉ ወደ ወልዋሎ ተመልሷል

ከቀናት በፊት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በስምምነት የተለያየው አማካዩ አፈወርቅ ሀይሉ ወደ ቀድሞ ክለቡ ወልዋሎ አምርቷል። ከዚ ቀደም በድሬ ፖሊስ ጨምሮ ወልዋሎ፣ ሀድያ ሆሳዕና፣ ባህርዳር ከተማ እንዲሁም ዋናው እና የኦሎምፒክ ብሄራዊ ቡድንን ማገልገል የቻለው አማካዩ ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ ካደረገ በኋላ ማረፍያው ወልዋሎ ሆኗል። ወልዋሎ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለማሳደግ ጉልህ ድርሻ ከተጫወቱ አንዱ የሆነው አማካዩ ቢጫዎቹን ለመቀላቀል ከተስማማ በኋላ የህክምና ምርመራውን ያጠናቀቀ ሲሆን በዛሬው ዕለት በይፋ የቀድሞ ክለቡን ተቀላቅሏል።

