ወልዋሎዎች አጥቂ አስፈረሙ

ወልዋሎዎች አጥቂ አስፈረሙ

ከቀናት በፊት ከሲዳማ ቡና ጋር የተለያየው ተጫዋች ወደ ቢጫዎቹ አምርቷል

ናይጄርያዊ አጥቂ ሳሙኤል አያንሪንዴ እና አማካዩ አፈወርቅ ሀይሉ ወደ ቡድናቸው የቀላቀሉት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ አጥቂው ተመስገን መንገሻን አስፈርመዋል። ከቀናት በፊት ላለፉት ስድስት ወራት ቆይታ ካደረገበት ሲዳማ ቡና በስምምነት የተለያየው ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም በአርባምንጭ ከተማ ፣ሰሜን ሸዋ ደብረብርሀን እንዲሁም በሲዳማ ቡና ከተጫወተ በኋላ ማረፊያዊ ወልዋሎ ሆኗል።