በመጀመሪያው ዙር የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የምትገጥመው ሳኦቶሜ ፕሪንስፔ ስብስቧን ይፋ አደረገች

ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በሚደረገው ፍልሚያ በመጀመሪያው ዙር የማጣሪያ ጨዋታ ከኢትዮጵያ ጋር የተደለደለችው ሳኦቶሚ ፕሪንስፔ ዋልያዎቹን የሚገጥመው ስብስቧን ይፋ አደርጋለች። የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ፖርቹጋላዊው ሪካርዶ ሞንሳንቶ በማጣርያ ጨዋታው የሚጠቀሟቸው 26 ተጫዋቾችን ይፋ ስያደርጉ በስብስቡም አስራ ስድስት የፖርቹጋል እና የስፔን ጥምር ዜግነት ያላቸውን ተጫዋቾች አካተዋል። በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ካደረጋቸው አስር ጨዋታዎች ዘጠኝ ሽንፈቶች አስተናግዶ በመጨረሻው ጨዋታ ማላዊን አንድ ለባዶ በማሸነፍ የምድቡ የመጨረሻ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው ብሔራዊ ቡድኑ መጋቢት 16 በድሬዳዋ ስታድየም ዋልያዎቹን በመግጠም የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድሩን ይጀምራል።

