ከነአን ማርክነህ የዋልያዎቹን ስብስብ መቼ ይቀላቀላል ?

ከነአን ማርክነህ የዋልያዎቹን ስብስብ መቼ ይቀላቀላል ?

በኦማን ድንቅ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው ከነአን ማርክነህ መቼ ብሔራዊ ቡድኑ እንደሚቀላቀል ታውቋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2027 አፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ለሚያደርጋቸው የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ ልምምዳቸውን እየሰሩ ይገኛሉ። ከኢትዮጵያ ውጭ የዋልያዎቹን ስብስብ እንዲቀላቀሉ ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከልም በኦማን ሊግ ለአል ሸባብ የሚጫወተው ከንዓን ማርክነህ ቡድኑን እንዳልተቀላቀለ ቀደም ብለን ባጋራናቹ መረጃ መጥቀሳችን ይታወሳል።

አሁን ባገኘነው መረጃ መሠረትም በኦማን ጂንዳል ሊግ ቆይታው 13 ግቦች እንዲሁም በአህጉራዊው ኤስያ ቻሌንጅ ሊግ በተከናወኑ ሦስት ጨዋታዎች 2 ግቦች እና 1 ግብ የሆነ ኳስ በማመቻቸት በክለቡ ጥሩ ውጤት የአምበሳውን ድርሻ በመወጣት ድንቅ ጊዜ በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ከንዓን ማርክነህ በዚህ ሳምንት አጋማሽ የሊግ ጨዋታውን ካደረገ በኋላ ሐሙስ መጋቢት 10 አዲስ አበባ ገብቶ ብሔራዊ ቡድኑን በመቀላቀል ረፋድ ላይ በሚኖረው ልምምድ እንደሚሳተፍ አውቀናል።