ኢትዮ ኤሌክትሪክ በከፍተኛ ሊጉ የደመቁ ተጫዋቾች ለማስፈረም ተስማማ

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በከፍተኛ ሊጉ የደመቁ ተጫዋቾች ለማስፈረም ተስማማ

በጣምራ አስራ ስድስት ግቦች ያስቆጠሩ ሁለት የደሴ ከተማ ተጫዋቾች ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አቀኑ

ከብዙዎች ግምት ውጭ የተሳካ የውድድር ዓመት አሳልፈው ተፎካካሪ ቡድን የገነቡትን የዋና አሰልጣኙ ዘሪሁን ሸንገታን ውል ለማራዘም ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ በዝውውሩ ተሳትፎ ሳያደርጉ ቆይተው በዛሬው ዕለት ፍራኦል መንግስቱን ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች በከፍተኛ ሊጉ ድንቅ የውድድር ዓመት ያሳለፉ ሁለት ተጫዋቾች ለማስፈረም ተስማምተዋል ፤ ቡድኑን ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሱት ደግሞ በከፍተኛ ሊጉ ደሴ ከተማ ቆይታ ያደረጉት የፊት መስመር ተጫዋቾች ሲሆኑ አስር ጎል በማስቆጠር የከፍተኛ ሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የሆነው አማኑኤል ግዛቸው እና ስድስት ግቦች ያስቆጠረው እሱባለው ሙሉጌታ ናቸው።