የፍራኦል መንግስቱ ማረፊያ ክለብ ታውቋል

የፍራኦል መንግስቱ ማረፊያ ክለብ ታውቋል

ከሲዳማ ቡና ጋር የሊጉን ዋንጫ ያሳካው ተከላካዩ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ኢትዮ ኤሌክትሪክን የተቀላቀለ የመጀመርያው ተጫዋች ሆኗል።

በዝውውር መስኮቱ ተሳትፎ ሳያደርጉ የቆዩት በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የሚመሩት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከሲዳማ ቡና ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ያነሳው የግራ መስመር ተከላካዩ ፍራኦል መንግስቱን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል። ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ቡና ቀጥሎም በሀድያ ሆሳዕና ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ ሀላባ ከተማ ፣ አዲስ አበባ ከተማ ፣ ባህር ዳር ከተማ የተጫወተው ተጫዋቹ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከሲዳማ ቡና ጋር ጥሩ ቆይታ ካደረገ በኋላ አሁን ደግሞ ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለማምራት ስምምነት ላይ ደርሷል።