ሀድያ ሆሳዕና አሰልጣኙን አግዷል

ሀድያ ሆሳዕና አሰልጣኙን አግዷል

በወጥ አቋም ላይ የማይገኙት ነብሮቹ አሰልጣኛቸውን ማገዳቸው አውቀናል።

በአሰልጣኝ ካሊድ መሐመድ እየተመሩ የሊጉ ጅማሬያቸውን አሳምረው የነበሩት ሀድያ ሆሳናዎች የሊጉ ጨዋታዎች እየገፉ ሲሄድ ከውጤት ጋር በተያያዘ ወጥ በሆነ መልኩ መጓዝ አለመቻሉን ተከትሎ በሊጉ ሰላሳ አራት ነጥብ በመያዝ አስራ አምስተኛ ደረጃ በመያዝ የወራጅ ስጋት ተደቅኖባቸዋል።

በዚህ ደስተኛ ያልሆኑት የክለቡ የበላይ አካላቶች ዋና አሰልጣኙን ካሊድ መሐመድን በማገድ በምትካቸው ሌላ አሰልጣኝ ለመቅጠር እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።