የአንደኛ ሊጉ ድምቀት ተስፈኛው ተከላካይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ተቀላቅሏል።

ከአብዲ ቦሩ እግርኳስ አካዳሚ ተገኝቶ በአንደኛ ሊግ ለፉሪ ክፍለ ከተማ እየተጫወተ የሚገኘው ተስፈኛው ተከላካይ ፉዓድ እንድሪስ ለንግድ ባንክ ለመጫወት ተስማምቷል።
አሰልጣኝ በጸሎት ከዚህ ቀደም በሊጉ ብዙም የማይታወቁ ተጫዋቾችን መልምለው በማምጣት የሚታወቁ ሲሆን አሁንም ደግሞ በሀገሪቱ የሊግ እርከን ሦስተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ከአንደኛ ሊግ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበውን ፉዓድን በቀጥታ ወደ ሊጉ በማምጣት አስፈርመውታል።

